Monday, August 8, 2016

እኔስ አለኝ Enies Alegn ዳግማዊ ጥላሁን

ዳግማዊ ጥላሁን Dagmawi Tilahun
አንደበቴ ፡ አይፈታም ፡ ሥራ
ለምሥጋና ፡ ስለ ፡ ተሰራ
የልቤ ፡ ሀሳብ ፡ የአፌ ፡ ቃል
አማረልኝ ፡ ዕልልታ ፡ ይዟል

አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x)

ሁሉም ፡ ነገር ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው
የሚታየው ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው
የሚሰማው ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው
ክብር ፡ ዝና ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው

አሃ ፡ አሃ ፡ አንተን ፡ ፈልጌ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ውስጤማ ፡ ናፍቆ
አሃ ፡ አሃ ፡ ፍቅርህ ፡ ገባብኝ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ በልቤ ፡ ዘልቆ
አሃ ፡ አሃ ፡ ይኸው ፡ ሽብሸባ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ለስምህ ፡ ጉዳይ
አሃ ፡ አሃ ፡ የእኔስ ፡ እልልታ ፡ አሃ ፡ አሃ ፡ ይሂድ ፡ ወደላይ

አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x)

አንተ ፡ በሰራኸው ፡ አልወስድም ፡ ምሥጋና
ልቤን ፡ ከፈትኩ ፡ እንጂ ፡ ምን ፡ አደረኩና
አንተ ፡ በሰራኸው ፡ አልወስድም ፡ ምሥጋና
እንኳን ፡ ተቀንሶ ፡ መቼ ፡ ይበቃና

ይኸው (፪x) ፡ ዕልልታው ፡ ይኸው (፪x)
ይኸው (፪x) ፡ ሽብሸባው ፡ ይኸው (፪x)
ይኸው (፪x) ፡ እልልታው ፡ ይኸው (፪x)
ይኸው (፪x) ፡ አምልኮው ፡ ይኸው (፪x)

ባለቤቱ ፡ የምሥጋና ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አለና
ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይኸውልህ ፡ ይኸው ፡ ጌታ
ባለቤቱ ፡ የምሥጋና ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አለና
ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይገባሀል ፡ የእኔ ፡ ጌታ

መሻቴ ፡ የእኔማ ፡ ደስታ ፡ የአምልኮ ፡ ሽታ
አላማ ፡ የመፈጠሬ ፡ ለዚህ ፡ ነው ፡ ላምልክ ፡ አብሬ
ቅሬታ ፡ የለም ፡ ትካዜ ፡ ምስጋናን ፡ ባሰብኩኝ ፡ ጊዜ

አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x)

አንደበቴ ፡ አይፈታም ፡ ሥራ
ለምሥጋና ፡ ስለ ፡ ተሰራ
የልቤ ፡ ሀሳብ ፡ የአፌ ፡ ቃል
አማረልኝ ፡ ዕልልታ ፡ ይዟል

አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x)

ሁሉም ፡ ነገር ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው
ገንዘብ ፡ ንብረት ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው
ስልጣን ፡ ሹመት ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው
ዘውዱ ፡ ንግሱ ፡ አላፊ ፡ ነው ፡ አምልኮ ፡ ግን ፡ ዘላቂ ፡ ነው

አዝ፦ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ እኔስ ፡ አለኝ (፬x)

ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይኸውልህ ፡ ይኸው ፡ ጌታ
ባለቤቱ ፡ የምሥጋና ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ አለና
ባለቤቱ ፡ የዕልልታ ፡ ይገባሀል ፡ የእኔ ፡ ጌታ