Monday, February 29, 2016

አቤት ምህረት የበዛለት Abet Mehret Yebezalet


 ዳንኤል አ/ሚካኤል Daneil A/Miche

አዝ፦ አቤት  ምሕረት  የበዛለት  እንደ  እኔ  ያለው
አቤት  ፀጋ  የበዛለት  እንደ  እኔ  ያለው
ያመስግንህ  እንጂ  ኦሆ
ስላደረግህለት  ሌላ  ምን  ቃል  አለው 

ሁሌ  በልቤ  እኔ  የምመኘው
አንተን  ማመስገን  ሥምህን  ማክበር  ነው
ዓይኔ  በርቶልኝ  የውስጥ  ሃሳቤ
ክብርህን  አይቼ  ልኑር  ጠግቤ

አንደበት ያለው  ሁሉ  ክቡር  ሥምህን  ከፍ ያድርገው
ክቡር ሥምህን ያመስግነው
ምሕረት ፀጋ የበዛለት ማዳንህን ይናገረው


ከአማልክት መሃል አንተ ብቻህን ጌታ ነህ
          አንተ ብቻህን አምላክ ነህ
-----አዝ------
ሁሌ በልቤ እኔ የምመኘው
አንተን ማመስገን ሥምህን ማክበር  ነው
ዓይኔ በርቶልኝ የውስጥ ሃሳቤ
አቤቱ ጌታ አምላክ  ሆይ
ወደ  አንተ እገሰግሳለሁ
ክብርህን ኃይልህን አይ ዘንድ
ይሄ ለእኔ ጥማቴ ነው

ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው
ልበል ሥምህን ላክብረው
የአንተ መክበር ለእኔ ደስታ ነው

      ------አዝ------