Wednesday, August 10, 2016

ይፈውስ ይዳሰኝ Yefewes Yedasegn እንዳለ ወልደጊዮርጊስ Endale Woldegiorgis #4

እንዳለ ወልደጊዮርጊስ Endale Woldegiorgis 


ሳትነካኝ ፡ ሳትነካኝ ፡ አልውጣ ፡ ከዚህ
ሳትነካኝ ፡ አልውጣ ፡ ከዚህ

አዝ፦ ይፈውስ ፡ ይዳሰኝ ፡ እጅህ (፬x)

እጅህ ፡ ነው ፡ የሚያጸናኝ ፡ የሚያጽናናኝ
እጅህ ፡ ነው ፡ ከስብራቴ ፡ ሚጠግነኝ
እጅህ ፡ ነው ፡ የሚያብስልኝ ፡ የልቤን ፡ እምባ
እጅህ ፡ ነው ፡ ደስታ ፡ ሚሰጠኝ ፡ ቤትህ ፡ ስገባ

አዝ፦ ይፈውስ ፡ ይዳሰኝ ፡ እጅህ (፬x)

ላይ ፡ ላዬን ፡ ሳይሆን ፡ ልቤን ፡ የሚነካው
ጢሻውን ፡ ውስጠቴን ፡ በፍቅር ፡ ሚያንኳኳ
ሚነቀል ፡ ነቅሎ ፡ ሚተከል ፡ ተክሎ
የሚለውጠኝ ፡ ሌላ ፡ አድርጐ
እጅህ ፡ እጅህ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ እጅህ
እጅህ ፡ እጅህ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ እጅህ

አዝ፦ ይፈውስ ፡ ይዳሰኝ ፡ እጅህ (፬x)