Well come to Holymezmur Lyrics blog :)
Peace be to you God's Family! Welcome to my Blog! In the first place I would like to thank you guys for visiting my blog.
I'm Eyob passionate web developer, programmer,graphic designer and blogger.
The thing that initiates me to start running this blog is the worship style followed by many churches in the mean time is not good. But this is all in my opinion; many songs are concatenated even some times songs that have no same message at all just because they are in the same rhythm utterly.
This problem is happening because most worship leaders in church didn't knew full lyrics of songs. So I came up with the idea to contribute something in order to see deep and lengthen worship not by singing bunch of concatenated songs, but......you get it!
I love to hear and sing songs very much. On this blog I would love to share lyrics of Amharic besides I am pretty sure that; this will benefit and help someone in God's kingdom especially worship leaders quoirs and all worshipers of God! If you want video lyrics you can subscribe to my Youtube channel HolyMezmur Lyrics.
I hope will love both the idea and my blog! Please Visit again! I appreciate if you have any comment you can email me or directly comment on this blog.
May God bless us with deep and truthful worship!!
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የእግዚአብሔር ቤተስቦች! እንኳን ወደዚህ Blog መጣችሁ!
በትንሹ ራሴን ለማስተዋወቅ ያክል ኢዮብ እባላለሁ የኮምፒውተር ሶፍትዌር ባለሙያ ነኝ ከምንም በላይ ደግሞ ዳግም የተወለድኩ ክርስቲያን ነኝ! ይህንን ያክል ስለራሴ ካልኩ ይህንን ጦማር (Blog) ለመጀመር ያነሳሳኝ ዋናው ነገር አሁን በብዙ ቤተክርስቲያኖች ያለው የዝማሬ አምልኮ አካሄድ ነው፡፡ ይህም ብዙ የተለያዩ መዝሙሮች አዝማች ብቻ እየተቀጣጠለ ቁጥሮች የማይዘመሩበት ሲሆን ይህም በከፍተኛ ሁኔታ እየተለመደ የመጣ መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዴ ሲብስ ደግሞ ጭራሽ በመልእክትም ሆነ በሀሳብ አብረው የማይሄዱ የተለያዩ መዝሙሮች አዝማች፤ ሪትማቸው ወይም የሙዚቃ ስልተ ምታቸው ተመሳሳይ ስለሁነ ብቻ ተቀጣጥለው ይዘመራሉ፡፡ በርግጥ ይህ ነገር ከሁላችሁም አይን የተሰወረ አይመስለኝም፡፡ ይህም ደግሞ ሙሉ የመዝሙሮቹን ሀሳብ እንዳንረዳ እና ጥልቅ ወደሆነ የአምልኮ መንፈስ ውስጥ እንዳንገባ ያደርገናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ፡ አንድ ስለ እየሱስ የመስቀል ፍቅር የሚናገር መዝሙር አየዘመርን ሌላ እግዚአብሔር በምድር ስለ ሰጠን ስኬት የሚያወሳ መዝሙር ቢቀጠልበት ፤ የመጀመሪያውን መዝሙር ቀጥሮች ብንዘምር ስለ መስቀሉ ይበልጥ እንድናስብ ያደርገናል ይህም ጥልቅ ወደሆነ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ምስጋና እንድናቀርብ ያስችለናል፡፡ በተቃራኒው ቁጥሮቹ ተትተው ከላይ የገለጽኩት መዝሙር ሲቀጠል ግን ምስጋናችን ጥልቀቱ ቀንሶ በምድር ስለተደረገልን ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እናንተም ሌሎች ብዙ ምሳሌዎች መጨመር ትችላላችሁ፡፡ ወይስ ይህ ዘመን ቁጥር የማይዘመርበት ነው?
በ HolyMezmur Lyrics youtube Channal ላይ ደግሞ የመዝሙሮችን ግጥም በ ቪዲዮ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ ይህም የአምልኮ መሪዎችን መዘምራንን እንዲሁም ሁሉንም እግዚአብሔርን አምላኪ እንደሚጠቅም አምናለሁ፡፡ ያላችሁን ምንም አይነት አስተያየት በ ኢሜል ወይም እዚሁ Blog ላይ
ይፃፉልኝ፡፡
እግዚአብሔር በእውነተኛ እና ጥልቅ አምልኮ ይባርከን!!!
|
Eyob GetanehBy Profession web Developer & Programmer. By Passion Bloger & Graphic Designer. |