Friday, August 5, 2016

አንተን ካገኘሁ ጀምሮ

 አገኘሁ ይደግ Agegnehu Yideg



አዝ፦ አንተን ፡ ካገኘሁ ፡ ጀምሮ
ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ አምሮ
የፍቅርህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት
የምህረትህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት (፪x)

የፈሰሰው ፡ ሠማያዊ ፡ ፀጋ
አኑሮኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋ
የመረጥከኝ ፡ ተባረክልኝ
የወደድከኝ ፡ ተባረክልኝ

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞተሃል
አበሳዬን ፡ ወስደሃል
ምን ፡ ልክፈልህ
እንዲያው ፡ ልገዛልህ (፪x)

ሰው ፡ ያረገኝ ፡ ፀጋህ ፡ ነው
ታሪኬን ፡ ለውጦ
ከሞት ፡ አስመልጦ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን (፪x)

አዝ፦ አንተን ፡ ካገኘሁ ፡ ጀምሮ
ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ አምሮ
የፍቅርህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት
የምህረትህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት (፪x)

የዓለም ፡ ክብር ፡ ሃብት ፡ አያጓጓኝም
ከአንተ ፡ አይበልጥብኝም
መርጬሃለሁ ፡ እከተልሃለሁ

የምህረትህ ፡ የፍቅርህ ፡ ብዛቱ
አልበረደም ፡ ግለቱ
ያዘምረኛል ፡ ተድላዬ ፡ ሆኖኛል
ያዘምረኛል ፡ ሞገሴ ፡ ሆኖኛል

ሰው ፡ ያረገኝ ፡ ፀጋህ ፡ ነው
ታሪኬን ፡ ለውጦ
ከሞት ፡ አስመልጦ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን (፪x)

አዝ፦ አንተን ፡ ካገኘሁ ፡ ጀምሮ
ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ አምሮ
የፍቅርህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት
የምህረትህን ፡ ብዛት ፡ አልችልም ፡ ልገልጻት

በመረቅህልኝ ፡ አዲስ ፡ ህያው ፡ መንገድ
ደስ ፡ እያለኝ ፡ ልራመድ
መጨረሻዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
መጨረሻዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ

የሩቅ ፡ አገር ፡ የፅዮን ፡ ተጓዥ ፡ ነን
በሠማይ ፡ አገር ፡ ያለኝ
ታድያለሁ ፡ አገሬ ፡ ገባለሁ
ታድያለሁ ፡ ዘለዓለም ፡ አርፋለሁ

ሃሌሉያ

ሰው ፡ ያረገኝ ፡ ፀጋህ ፡ ነው
ታሪኬን ፡ ለውጦ
ከሞት ፡ አስመልጦ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመስገን (፪x)