Tuesday, June 13, 2017

ምን ይሆን ነበረ እጣዬ... አስቴር አበበ Aster Abebe #New Song Full Lyrics

Aster Abebe አስቴር አበበ #1
ፈልጌህ ፡ አላጣሁህም
ከልቤ ፡ ሽቼህ ፡ ራስህን ፡ አልሰወርክም (፪x)

ውሃ ፡ በሌለበት ፡ በደረቅ ፡ ምድር
ነፍሴ ፡ ተጠምታ ፡ አገኘችህ ፡ አገኘችህ ፡ አገኘችህ (፪x)

በቅቤና ፡ በስብ ፡ እንደሚረካ ፡ ሰው
ሳገኝህ ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው (፪x)

ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አባትነትህ
ዘላለም ፡ በቤቴ ፡ እራስ ፡ ሁን ፡ የምልህ
ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አምላክነትህ
ዘላለም ፡ በላዬ ፡ ንገስብኝ ፡ ምልህ

አዛኝ ፡ ባትሆን ፡ ፍቅር ፡ ባትሆን
አምላኬ ፡ ባትሆን ፡ ጌታዬ ፡ ባትሆን
ባትሸከመኝ ፡ በፍቅር ፡ ባትይዘኝ
ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡ መክረህ ፡ ባትመልሰኝ
በፍቅር ፡ ባትይዘኝ ፡ ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡ ምክርህ ፡ ባይደግፈኝ
ምን ፡ ይሆን ፡ ነበረ ፡ እጣዬ
ስለ ፡ ምሕረትህ ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ (፪x)

አቅም ፡ የሆንክልኝ ፡ ተባረክ
ዘውዴ ፡ መድመቂያዬ ፡ ተባረክ
ቅድስናዬ ፡ ነህ ፡ ተባረክ
አብ ፡ ፊት ፡ መታዪያዬ ፡ ተባረክ (፪x)

ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ
ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ

እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ በሙሉ ፡ ቀሪ ፡ ነው (፫x)
ሁሌ ፡ ምናፍቀው ፡ አንተን ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ በሙሉ ፡ ቀሪ ፡ ነው (፫x)

እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው
ሌላው ፡ በሙሉ ፡ ቀሪ ፡ ነው
እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው
ሌላው ፡ በሙሉ ፡ ቀሪ ፡ ነው
ቀሪ ፡ ነው (፮x)