ደረጀ ሙላቱ Dereje Mulatu
ነቀፋ ፡ ቢበዛ
አጃቢ ፡ ቢታጣ ያልተጠባበቅነው ፡ መከራ ፡ ቢመጣ ዕርፉን ፡ ጥለን ፡ አንዴ ወደ ፡ ሌላም ፡ ሩጫ የእግዚአብሔር ፡ ሥም ፡ ብቻ ይሁነን ፡ ማምለጫ ይህን ፡ ቀን ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ! አ ት ዘ ና ጊ ! ቃልኪዳንሽን ፡ ይዘሽ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ! <አዝ ፤ > ነፍሴ ፡ ሆይ! ኢየሱስን ፡ ስንቀበል ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር? ነፍሴ ፡ ሆይ! ኢየሱስን ፡ ስንቀበል ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል አንቱ ፡ መባል ፡ ሳይጀመር ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር? ፪) ዝና ፡ ቢበዛልን ፤ ስማችን ፡ ቢወጣ ዕልፍ ፡ ገዳይ ፡ ተብሎ ፡ ዘፈንም ፡ ቢመጣ ሰማይ ፡ ላንቀይር ፡ ማንም ፡ ላይ ፡ ሳንኮራ በትዕግሥት ፡ እንፈጽም ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ሥራ አንዴም ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ! አትዘናጊ! ለቃል ፡ ኪዳንሽ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ! <አዝ ፤ > ነፍሴ ፡ ሆይ! ኢየሱስን ፡ ስንቀበል ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር? ከተማ ፡ መግባት ፡ ሳይመጣ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር? ፫) መውጊያው ፡ ይነሣልን ፡ ብለን ፡ ስንለምነው ብሎ ፡ የሚመልስልን ፡ ፀጋዬ ፡ በቂ ፡ ነው እኛም ፡ እንደጳውሎስ ፡ እንኑር ፡ በጽናት የእግዚአብሔርን ፡ መንግሥት ፡ በግብር ፡ ልንወርሳት ግድየለም ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ ! አትዘግዪ ለቃልኪዳንሽ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ! <አዝ ፤ > ነፍሴ ፡ ሆይ! ኢየሱስን ፡ ስንቀበል ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር? ፬) ዕውነትን ፡ በውሸት ፡ የሚቀላቅሉ ነጩን ፡ ካድ ፡ አድርገው ፡ ጥቁር ፡ ነው ፡ የሚሉ ለጥቅም ፡ ያደሩ ፡ ወገኖች ፡ ቢነሡ እኛ ፡ በታማኝነት ፡ እንኑር ፡ ለንጉሡ አይደለም ፡ እንዴ ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ! አትዘናጊ! በፊርማችን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ትጊ! <አዝ ፤ > ነፍሴ ፡ ሆይ! ኢየሱስን ፡ ስንቀበል ከዚያም ፡ ደግሞ ፡ ለማገልገል ክብር ፡ ዝናው ፡ ሳይጀመር ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር? አገር ፡ መዞር ፡ ሳይጀመር ጓዳ ፡ እያለን ፡ የተባባልነው ፡ ምን ፡ ነበር? ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ የተገባባነው ፡ ቃልኪዳን ፡ ይከበር! |