Tuesday, September 6, 2016

ምህረቱ አያልቅምና Meheretu Ayalqemena ተስፋዬ ጋቢሶ

ተስፋዬ  ጋቢሶ Tesfaye Gabiso 
በባቢሎን ፡ ወንዞች ፡ ማዶ ፡ አዝነን ፡ ተቀምጠን
ጽዮንን ፡ ባሰብናት ፡ ጊዜ ፡ እጅግ ፡ አለቀስን
የመጽናናት ፡ አምላክ ፡ ከላይ ፡ ግን ፡ ያየናል
እንባችንን ፡ ጠርጐ ፡ ስብራታችንን ፡ ይጠግንልናል

አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
በክንዱ ፡ ለሚጐበኘን
መልካሙን ፡ መዓዛ ፡ በምሥጋና ፡ አቅርቡለት
በዕልልታ ፡ ስገዱለት

የችግረኞችን ፡ ጩኸት ፡ ሰምቶ ፡ አይጨክንም
ምርጦቹን ፡ ኧረ ፡ በፍፁም ፡ አያስጨንቅም
ጠላታቸው ፡ ሊበትን ፡ በነጐድጓድ ፡ አንቀጥቅጦ
ረድኤታቸው ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ ከጸባኦት ፡ በግርማው ፡ ተገልጦ

አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
በክንዱ ፡ ለሚጐበኘን
መልካሙን ፡ መዓዛ ፡ በምሥጋና ፡ አቅርቡለት
በዕልልታ ፡ ስገዱለት

በሥጋዎቻቸው ፡ የገነኑ ፡ ፈፅመው ፡ ሲወድቁ
እግዚአብሔርን ፡ በመታመን ፡ የሚጠባበቁ
በእንባቸው ፡ ፍሬ ፡ እያሸበርቁ
በክንፍ ፡ ይወጣሉ ፡ ይሮጣሉ ፡ ይገባሉ ፡ እንደ ፡ ዕንቁ

አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
በክንዱ ፡ ለሚጐበኘን
መልካሙን ፡ መዓዛ ፡ በምሥጋና ፡ አቅርቡለት
በዕልልታ ፡ ስገዱለት

ለእኛ ፡ መጠጊያችን ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔራችን
በምንም ፡ አንፈራም ፡ እርሱ ፡ ኃይላችን
ከሰይጣን ፡ አሰራር ፡ ሥሙ ፡ ይጠብቀናል
ለአሞራም ፡ ሳይሰጠን ፡ በክንፎቹ ፡ አዝሎ ፡ ቤቱ ፡ ያገባናል

አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
በክንዱ ፡ ለሚጐበኘን
መልካሙን ፡ መዓዛ ፡ በምሥጋና ፡ አቅርቡለት
በዕልልታ ፡ ስገዱለት (፪x)