ኢየሱስ ፡ ስለእኛ ፡ መስቀል ፡ ተሸክሞ
ቀራንዮ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ በጅራፍ ፡ ተገርፎጐልጐታ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ በግፍ ፡ ተሰቀለ
እንደጅራት ፡ ደሙ ፡ በሜዳ ፡ ፈሰሰ
ሞተ ፡ ተቀበረ ፡ ተስፋ ፡ የለው ፡ ብለው
ተከታይ ፡ ልጆቹ ፡ በሃዘን ፡ ተመተው
አዳኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ በክብር ፡ ተነሳ
ከሙታን ፡ አለት ፡ ውስጥ ፡ እኛንም ፡ አስነሳን
በትንሳኤው ፡ ኃይል ፡ ማሸነፍ ፡ ያገኙ
ከሞት ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ የተሸጋገሩ
የከበረ ፡ ሠማይ ፡ ይጠብቃቸዋል
በ. (1) .ቸው ፡ ሁሌ ፡ በእዚያ ፡ ይሆናል
ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በጌታችን ፡ ደም
በደል ፡ ተሰረየ ፡ በመሲሁ ፡ ደም
የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አይታሰብም
ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድሃኒዓለም
የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አያገኘንም
ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድኃኒዓለም
ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በመሲሁ ፡ ደም
በደል ፡ ተሰረየ ፡ በጌታችን ፡ ደም
የዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አይታሰብም
ክቡር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ለመድሃኒዓለም (፪x)
አማኑኤል ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፬x)
መዳናችን ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)
አማኑኤል ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፬x)
መዳናችን ፡ በእርሱ ፡ ነው (፫x)