አዲሱ ወርቁ Adisu Worku
ኮብልላ ፡ ነበረች ፡ ነፍሴ ፡ ከእግዜር ፡ መንገድ
በጣም ፡ የበደልኩኝ ፡ ኀጢአተኛም ፡ ነበርኩ
ግን ፡ አዳኜ ፡ ከላይ ፡ ፍቅሩን ፡ ሰጠኝ ፡ ሰላም
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ
አዝ፦ ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን ፡ አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ
ተስፋ ፡ ቢስ ፡ ነበርኩኝ ፡ ሊያወጣኝ ፡ ሲመጣ
ግን ፡ እርሱ ፡ ነገረኝ ፡ ነጻ ፡ እንደምወጣ
ከዚያማ ፡ አነሳና ፡ ክብሩን ፡ አቀናጀኝ
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ
አዝ፦ ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን ፡ አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ
ልቤን ፡ ደስ ፡ ይለዋል ፡ ከመረጥኩት ፡ ወዲህ
ከማዕበሉ ፡ አሁን ፡ ወዴርሱ ፡ ሸሻለሁ
ክንዱን ፡ ከተደገፍኩ ፡ አልፈራም ፡ መከራን
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ
አዝ፦ ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን ፡ አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ
ሰማያዊ ፡ ደስታን ፡ ሰላምን ፡ ከሰጠኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ለአንተ ፡ ሰጣለሁኝ
እንግዲህ ፡ እጄን ፡ እየያዝክ ፡ ከአንተም ፡ ጋር ፡ አቁመኝ
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ ልኮ ፡ አወጣኝ
አዝ፦ ደሙን ፡ ለእኔ ፡ አፍሶ ፡ አዳነኝ (፪x)
የማልረባም ፡ ብሆን ፡ አምላኬን ፡ የማላውቅ
ልጁ ፡ ለእኔ ፡ ወርዶ ፡ አወጣኝ