Friday, August 5, 2016

አምላኬ ደስታዬ Amlakie Destayie ዮሐንስ ግርማ Yohannes Girma

ዮሐንስ  ግርማ Yohannes Girma
ከቶ ፡ እንበለስ ፡ ባያፍራ
ከወይንም ፡ ሃረግ ፡ ላይ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ
የወይራ ፡ ሥራ ፡ ቢጐድል
እርሾችም ፡ መብልን ፡ ባይሰጡ

እኔ ፡ ግን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ
ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃይሌ ፡ ነው
እግሮቼን ፡ እንደ ፡ ዋላ ፡ እግሮች ፡ ያበረታ
በፍታዎች ፡ ላይ ፡ ያስኬደኛል (፪x)

አምላኬ ፡ ደስታዬ ፡ ደስታዬ ፡ ነህ
ኢየሱሴ ፡ ሙላቴ ፡ እርካታዬ ፡ ነህ (፪x)

በልጠኸኛል ፡ ሌላም ፡ አልፈልግም
ቀረም ፡ የምለው ፡ ነገርም ፡ የለኝ
ታምኜብህ ፡ በሁሉ ፡ ነገሬ
ይዤ ፡ መጣሁ ፡ የከንፈሬን ፡ ፍሬ (፪x)

ምን ፡ ይከብደው ፡ ብዬ ፡ ለየትኛው ፡ ልፍራ
ምን ፡ ያቅተውና ፡ ምኑን ፡ ብዬ ፡ ልፍራ (፪x)

ተራራ ፡ ላይ ፡ ማዳን ፡ የቻለው
ሸለቆው ፡ ውስጥ ፡ ኃይል ፡ የእርሱ ፡ ነው
ሁሉን ፡ የሚችል ፡ ሥሙ ፡ ኤልሻዳይ
የእኔ ፡ አምላክ ፡ ያለ ፡ በሰማይ (፪x)

እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል
የሕዝቡ ፡ መከታ ፡ ፅኑ ፡ ጋሻ ፡ ሆኗል (፪x)

መመኪያ ፡ ነው ፡ ለትውልድ ፡ ትምክህት
መጓደጃ ፡ የልጅ ፡ ልጅ ፡ ኩራት
የሚታመኑት ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይላሉ
ለዘለዓለም ፡ ማዳኑን ፡ ያያሉ

ከቶ ፡ እንበለስ ፡ ባያፍራ
ከወይንም ፡ ሃረግ ፡ ላይ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ
የወይራ ፡ ሥራ ፡ ቢጐድል
እርሾችም ፡ መብልን ፡ ባይሰጡ

እኔ ፡ ግን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ ይለእኛል
በመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ
ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃይሌ ፡ ነው
እግሮቼን ፡ እንደ ፡ ዋላ ፡ እግሮች ፡ ያበረታ
በፍታዎች ፡ ላይ ፡ ያስኬደኛል (፪x)