Friday, March 4, 2016

የሮጡለትን ያዩታል Yerotuleten Yayutal

ሀና  ተክሌ Hanna Tekle

ከአንተ በፊት የቆሰሉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ
እንደ  እኔና እንደ አንተ በነጻነት ዘመን ያልተፈጠሩ
ከአንቺ በፊት የተሰዉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ
እንደ እኔና  እንደ  አንቺ በነጻነት ዘመን  ያልተፈጠሩ

       ከእኛ  በፊት  ብዙ  አሉ  የተሰዉ ለወንጌሉ
       እንደ እኛ በነጻነት  ዘመን ያልተፈጠሩ
       ሳይሉ ችግሬን ጨርቄን  ማቄን  በጽድቅ የኖሩ
       በጌታ  የተጉ ለጌታ  የኖሩ  በሰው  የተጠሉ

አቤት የሮጡለትን  ያዩታል  ከወደላይ
የክብሩ  ጌታ  ሲያከብራቸው በሠማይ
አቤት  ያዩታል  ጌታን ፊት ለፊት
ሳያዩት  ያመኑትን  የናፈቁትን
በነፍሳቸው  የጨከኑት በሥጋቸው  ያከበሩት
አይገኝም  አክሊላቸው  በሠማይ ነው  ክፍያቸው
አቤት  የሮጡለትን  ያዩታል ከወደላይ

     ሆነው የባርነት  ባሪያ  ወጥተው ከሰውነት  ተራ
     የእኔ የሚሉት  የሌላቸው  ልሩጥ ለእኔም ማያቃቸው
    ለወንጌል  የቆሙ  ለወንጌል  የቀኑ
   ገንዘብ  የማይደፍራቸው  ሰልፍ  ብርታታቸው

አቤት የሮጡለትን  ያዩታል ከወደላይ
የክብሩ  ጌታ  ሲያከብራቸው በሠማይ
አቤት  ያዩታል  ጌታን  ፊት ለፊት
ሳያዩት ያመኑትን  የናፈቁት
በነፍሳቸው  የጨከኑት በሥጋቸው ያከበሩት
አይገኝም  አክሊላቸው  በሠማይ ነው  ክፍያቸው
አቤት  ያዩታል  ጌታን ፊት  ለፊት

     ማነው  ታዲያ  የዘምኔ  አርበኛ
     ለጌታ ነገር ያልተኛ
    ብድራቱንስ ያልተቀበለ
    እውነት  ለወንጌል የጨከነ
    በነጻነት ዘመን  ራሱን  የሰዋ
    ለጥቅም  ያልኖረ  በእምነቱ የጸና

ማነው  የዘምኔ  ወንጌል  ነጋሪ
በተግባር የታየ  የጽድቅ  ተባባሪ
ያልሆነ  በፍፁም  የነጻነት  ባሪያ
ከቶ ያልተገኘ  እዚህ  ሲሉት እዚያ
ማነው የአቋም ሰው  ዘመን  ተሻጋሪ
ሰልፍ እየበረታ  ወንጌሉን  ዘማሪ

      ማነው  የዘመኔ  ባለ  አክሊል ተረኛ
     ለራሱ ያልኖረ  ከሥጋው ጠበኛ
    ሞትን  ጥቅሜ ብሎ በነፍሱ  የጨከነ
    ግራ  ቀኝ ያላየ  ለቃሉ  የታመነ
    ማነው የዘምኔ  አርበኛ  ማነው

አቤት  የሮጡለትም  ያዩታል ከወደላይ
የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው  በሠማይ