Wednesday, March 9, 2016

አልተማረም አሉኝ Altemarem Alugn

ዶ/ር ደረጀ  ከበደ Dr. Dereje Kebede


የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ሳይንስ ፡ አይጨብጠው
የእብድ ፡ ቃላት ፡ ብዛት ፡ በእውነት ፡ አይገምተው
መስፈሳዊ ፡ አይኖች ፡ ተከፍተው ፡ ካላዩት
ቃሉን ፡ ሞኝነት ፡ ነው ፡ አውቀናል ፡ ለሚሉት

               ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ
               ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ
               ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው
               እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x)

         ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ
         የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ
         ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x)
         የሚጠፋ ፡ ጥሪት ፡ ማከማቸት ፡ ትቼ
         ዘላለማዊውን ፡ ለማግኘት ፡ ዘይጄ
         ጌታዬን ፡ የሙጥኝ ፡ ብዬ ፡ መወሰኔ
         ከአዋቂዎች ፡ በላይ ፡ አልሆንኩም ፡ ወይ ፡ እኔ
         ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ
         ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ
         ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው
         እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x)

ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ
ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x)


       ምድር ፡ እና ፡ ሰማይን ፡ ያበጀው ፡ ፈጣሪ
        አይመረመርም ፡ ገብቶ ፡ ልብራቶሪ
       ቁጥርን ፡ ከቁጥር ፡ ጋር ፡ ሲያጋጩ ፡ ቢኖሩ
       አያዩትም ፡ ጌታን ፡ እሩቅ ፡ ነው ፡ ሃገሩ

ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ
ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ
ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው
እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x)
ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ
ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x)
ሰአቱ ፡ ገና ፡ አለ ፡ ጊዜአችን ፡ አልከፋም
እግዚአብሔር ፡ ደጁን ፡ በሰው ፡ ልጅ ፡ አልዘጋም
ከማንቀላፋቱ ፡ ነቅቶ ፡ ለታረመ
ብርሃን ፡ ነው ፡ ገና ፡ ዛሬ ፡ መች ፡ ጨለመ

   ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ
   ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ
   ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው
   እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x)
   ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ
   የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ
   ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x)