Friday, March 4, 2016

በዚህ ዓለም Bezihech Alem


ሳሙኤል  ንጉሤ Samuel Negussie


በዚህ ዓለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር  አለ
ከአንተ ጋር  አንደመኖር
በዚህ ምድር ምን  ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር አንደመኖር
እወደዋለሁ ሕይወቴን  እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ

         በአንተ ዘንድ ያለን የህይወት ቃል
         ሌላ ስፍራ የትም ማላገኘው
         ብር የማይሰጠኝ ወርቅ የማይሰጠኝ
         የሕይወቴን አቅጣጫ  የለወጠው

የሁልጊዜ ነው የልቤ  ሰላም
ከመንፈስህ ከቃልህ የመነጨው
በዚህ አለም ነገር የማይወሰን
የእኔን ሕይወት የደስታ ያደረገው

      ብዙ ደስታ አለ በሕይወቴ
     ብዙ ሰላም አለ  በሕይወቴ
     ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር  ስላለ
     መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ

ሸክም የከበደው ወደ እኔ  ይምጣ
ይረፍ ብለህ  የጠራኸኝ አንተ  እኮ ነህ
ሁሉንም ነገር ለ አንተ ሰጥቼ
እፎይ ብዬ ተደላድዬ ምኖርብህ

      ኢየሱስ ከአንተ ጋር ያለኝ ህብረት
     ማለት ለእኔ አለሜ ነው
     ለሕይወቴ ትርጉም ያገኘሁበት
    ምክኒያቱ ነው የዘላለሜ  የሰመረበት