Wednesday, August 17, 2016

በመጀመሪያ ላመስግንህ Bemejemeriya Lamesgeneh ሳሙኤል ተስፋሚካኤል Samuel Tesfamichael #1

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል Samuel Tesfamichael

አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ ላመስግንህ ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልጀምር
በመሃከልም ፡ ልጨማምርበት ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልቀጥል
በመጨረሻ ፡ መደምደሚያዬ ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ
በመጨረሻ ፡ በመቋጫዬ ፡ ዝማሬ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ (፪x)

ያረክልኝ ፡ ነገር ፡ በዝቶ ፡ ስለምን ፡ ፊትህ ፡ ላጉረምርም
አፌን ፡ በምሥጋና ፡ ልክፈት ፡ ማዘን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አያምርም
ይኸው ፡ ምሥጋና ፡ ይኸው ፡ ዝማሬ ፡ አቀርባለሁ ፡ ዛሬ
ይኸው ፡ ዕልልታ ፡ ይኸው ፡ ስግደቴ ፡ ለመድሃኒቴ

አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ ላመስግንህ ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልጀምር
በመሃከልም ፡ ልጨማምርበት ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልቀጥል
በመጨረሻ ፡ መደምደሚያዬ ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ
በመጨረሻ ፡ በመቋጫዬ ፡ ዝማሬ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ (፪x)

ብዙ ፡ ነገር ፡ አርገህልኝ ፡ ጥቂቱን ፡ ብትከለክለኝ
ያውም ፡ ለጥቅሜ ፡ ብለህ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ ለጉዳት ፡ አሰብክብኝ
በግማሽ ፡ ልቤ ፡ ምሥጋና ፡ አልሰጥም ፡ እኔ ፡ አልዘምርም
ገብቶኛል ፡ የአንተ ፡ የአምላኬ ፡ አላማ ፡ ይኸው ፡ ምሥጋና

አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ ላመስግንህ ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልጀምር
በመሃከልም ፡ ልጨማምርበት ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልቀጥል
በመጨረሻ ፡ መደምደሚያዬ ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ
በመጨረሻ ፡ በመቋጫዬ ፡ ዝማሬ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ (፪x)

አፌን ፡ ስከፍት ፡ በምሥጋና ፡ ሳቀርብ ፡ ለጌታ ፡ ሲሰጠኝ
ማጉረምረም ፡ ማዘን ፡ መቆዘም ፡ አላገኙኝም ፡ ፈልገው
ለቀው ፡ ይጠፉ ፡ ብቻዬን ፡ ቀረሁ ፡ ሰላም ፡ አገኘሁ
ገና ፡ ያጡኛል ፡ ሳቀርብ ፡ ምሥጋና ፡ ላብዛ ፡ እንደገና

አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ ላመስግንህ ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልጀምር
በመሃከልም ፡ ልጨማምርበት ፡ ስለምን ፡ በሌላ ፡ ልቀጥል
በመጨረሻ ፡ መደምደሚያዬ ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ
በመጨረሻ ፡ በመቋጫዬ ፡ ዝማሬ ፡ ይኸው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ (፪x)