Monday, August 8, 2016

ሁሉም ይስማ Hulum Yesma ኬፋ ሚደቅሳ

ኬፋ ሚደቅሳ Kefa Mideksa

አዝ፦ አንተ ፡ እንደ ፡ ረዳኸኝ
አንተ ፡ እንዳነሳኸኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ (፪x)

ምደረ ፡ በዳውን ፡ አቋርጫለሁ
እጄን ፡ ይዘኸኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በሕይወት ፡ ኖሪያለሁ
አልነደፈኝም ፡ እባቡ ፡ ጊንጡ
አቤት ፡ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ተረፍኩ ፡ ከስንቱ (፪x)
አቤት ፡ አባቴ ፡ በአንተ ፡ ተረፍኩ ፡ ከስንቱ

ሲጨላልም ፡ የማይነጋ ፡ ሲመስል
የቅርብ ፡ የሩቅ ፡ ገለል ፡ ገለል ፡ ሲል
በውድቅቱ ፡ ሌሊቱ ፡ መጣህና
በሰልፍ ፡ ቀን ፡ ራሴን ፡ ሸፈንክና

አሰመርከኝ (፫x)
እንዳዳንኩህ ፡ እንዳገዝኩህ ፡ መስክር ፡ አልከኝ
አባት ፡ ሆንከኝ ፡ ክብር ፡ ሆንከኝ ፡ ተሸከምከኝ
በደግጬ ፡ እቅፍ ፡ አርገህ ፡ አነሳኸኝ

በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤት ፡ አግብተኸኛል ፡ አሃሃ (፪x)
ቤት ፡ አግብተኸኛል
በፊትህ ፡ ቃል ፡ ደስታ ፡ ለእኔ ፡ ሰጥተኸኛል ፡ አሃሃ (፪x)
ለእኔ ፡ ሰጥተኸኛል
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ የማመሰግንህ ፡ ምክኒያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አሃሃ (፪x)
ምክኒያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
ከዛ ፡ ከጨካኙ ፡ ነፍሴን ፡ ከሚፈልግ ፡ ከአውሬ ፡ አስጥለኸኝ ፡ ነው ፡ አሃሃ (፪x)
ከአውሬ ፡ አስጥለኸኝ ፡ ነው

አዝ፦ አንተ ፡ እንደ ፡ ረዳኸኝ
አንተ ፡ እንዳነሳኸኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ (፪x)