ወርቅነህ አላሮ Workneh Alaro
አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አበሳዬን ፡ ሁሉ ፡ አራቀ እድፋሙን ፡ ልብሴን ፡ ቀየረው (፪x) ሰይጣንን ፡ ገሰጸው እርሱ ፡ እኮ ፡ ልጄ ፡ ነው ፡ አለው የእኔ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ አባረረው አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ጠላት ፡ ዘባበተብኝ አምላክህ ፡ እስቲ ፡ ያድንህ ፡ አለኝ መጨረሻህ ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ አለኝ የተዋረዱትን ፡ የሚያይ ፡ ከተፍ ፡ አለልኝ ፡ ከሰማይ እንደእርሱ ፡ ማነው ፡ ኤልሻዳይ አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ ለካ ፡ መልስ ፡ አለው ዙሪያዬን ፡ ለከበበኝ ሊወግረኝ ፡ ድንጋይ ፡ ላነሳን አቤት ፡ የማዳን ፡ ጥበቡ የማይመረመር ፡ ነው ፡ ፍርዱ በዕልልታ ፡ ለእርሱ ፡ ስገዱ አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ሰይጣን ፡ በብርቱ ፡ ከሰሰኝ በኀጢአቴ ፡ እንዲፈረድብኝ ____ ፡ እንዲ ፡ ____ ፡ ከበበ ጠበቃዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ቆመልኝ በደሙ ፡ አስተሰረየልኝ (፪x) አዝ፦ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ያለኝ ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የራራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው |