Monday, August 15, 2016

ለአንተ ብቻ Lante Becha አሃቫ የወንጌል መዘምራን Ahava Gospo Singers

አሃቫ  የወንጌል መዘምራን Ahava Gospo Singers

ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)

በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ
ስለ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ይተረካል
ለሕያውም ፡ ለግዑዙም ፡ ዜማ ፡ ይቀመራል
ሁሉም ፡ በእራሱ ፡ መንገድ ፡ ይጓዛል ፡ ይሮጣል
የወደደውን ፡ መርጦ ፡ ያወድሳል

አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ ከሁሉም ፡ አንተን ፡ መርጫለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ እቀኝልሃለሁ
የእኔ ፡ ዜማ ፡ ዝማሬ ፡ የሚገባው
የመዳኔ ፡ ብቸኛ ፡ መንገድ ፡ የሆንህ

ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)

አንዱም ፡ ተነሳ ፡ የዜማ ፡ እቃውን ፡ ቃኘ
ድምፁን ፡ ከፍ ፡ አድርጐ ፡ ለሚያልፈው ፡ ተቀኘ
ሌሎችም ፡ አብረው ፡ በአንድነት ፡ ተስማምተው
(ሁሉም ፡ በአንድ ፡ ልብ ፡ ህብረት ፡ ሆነው)
ውዳሴን ፡ አሰሙ ፡ ለሚያልፈው

አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ መርጫለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ እቀኝልሃለሁ
የእኔ ፡ ዜማ ፡ ዝማሬ ፡ የሚገባው
የመዳኔ ፡ ብቸኛ ፡ መንገድ ፡ የሆንህ

ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)
ለአንተ ፡ ብቻ (፯x)

ኦዎኦ (፲፪x)

ምሥጋናዬ ፡ (ኦ)
አምልኮዬን ፡ (ኦ)
አቀርባለው ፡ ለአንተ ፡ ዝማሬዬን (፮x)