Friday, August 12, 2016

ሽልማቴ ነህ Shilimateh Neh መሥፍን ማሞ Mesfin Mamo #1

መሥፍን  ማሞ  Mesfin Mamo


ሁሉንም ፡ ትቼ ፡ እሮጣለሁ
ያለኝንም ፡ ሁሉ ፡ አጣዋለሁ
የሚጠቅመኝንም ፡ እተዋለሁ
ብቻ ፡ አንድ ፡ ነገር
አንድ ፡ ነገር ፡ እሻለሁ
እርሱንም ፡ አውቃለሁ

ሁሉም ፡ ቀርቶብኝ ፡ ቢገኝልኝ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ ፡ የናፈቀኝ
በእርሱ ፡ ተገኝቼ ፡ እርሱንም ፡ አግኝቼ
ሌላ ፡ መሻት ፡ የለኝ ፡ የምራበው
ኢየሱስ ፡ ዕንቁዬ ፡ ነው

እርሱን ፡ ከማወቅ ፡ ጋር ፡ ምን ፡ ይወዳደራል
ሁሉን ፡ እርግፍ ፡ አድርጐ ፡ አስትቶ ፡ ያስኬዳል
ሽልማቴ ፡ ሌላ ፡ መች ፡ ለእኔ ፡ ሆነልኝ
እርሱ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ እኔን ፡ የወደደኝ (፪x)

ሽልማቴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ሽልማቴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ (፪x)

ሆነህ ፡ ተገኝተሃል ፡ በእኔ ፡ ዘንድ ፡ አንደኛ
ሁሉንም ፡ አስናቅከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ እረኛ (፪x)

የከበረ ፡ የገነነ ፡ እኔ ፡ ምሻው
ኢየሱስ ፡ ነው (፲፪x)