Wednesday, September 7, 2016

አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ...Ante Yenie መስፍን ጉቱ Mesfin Gutu #3

 መስፍን  ጉቱ  Mesfin Gutu #3
አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ
ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ
በጨለማ ፡ እኔ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ
ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፣ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ (፪x)

ማን ፣ ኧረ ፡ ማን ፣ ማን ይወስድብኛል ፡ አንተን ፡ ከኔ (፪x)
ማን ፣ ኧረ ፡ ማን ፣ ማን ይወስድብኛል ፡ አንተን ፡ ከኔ (፪x)
ተማመለህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
በጭንቅ ፡ የወለድከኝ ፡ በጎልጎታ
እድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ሰጥሃለሁ
ዘላለም ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ፣ እገዛለሁ

ታዲያ ፣ ልዘምር ፡ እንጂ
ልቀኝ ፡ እንጂ
ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አሃሃሃ
ታዲያ ፡ ታዲያ (፪x)

እንደመሸ ፡ አይቀርም ፡ ለሊቱ ፡ ይነጋል (፬x)
ማንጋት ፡ ልማድህ ፡ ነውና ፣ ማንሳት ፡ ልማድህ ፡ ነወና
ማክበር ፡ ልማድህ ፡ ነወና ፣ ማስዋብ ፡ ልማድህ ፡ ነውና

ውዴ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ ደግሞ ፡ የእርሱ ፡ ነኝ ፡ የየሱስ ፡ ነኝ (፪x)
ማንም ፡ አይገባም ፡ በመሀላችን
ጉድለት ፡ የሌለበት ፡ ነው ፡ ፍቅራችን
ጊዜም ፡ ሁኔታም ፡ አይሽረዉም ፡ ለኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ልዩ ፡ ነዉ ፣ ልዩ ፡ ነዉ

ታዲያ ፣ ልዘምር ፡ እንጂ
ልቀኝ ፡ እንጂ
ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አሃሃሃ
ታዲያ ፡ ታዲያ (፪x)

አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ
ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ
በጨለማ ፡ እኔ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ
ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፣ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ (፪x)