Tuesday, September 6, 2016

የማይሆነው ላይሆን Yemayhonew Layhon ቃልኪዳን ጥላሁን

ቃልኪዳን ጥላሁን [Lily Tilahun]

የማይሆነው ፡ ላይሆን ፡ የሚሆነው ፡ ላይቀር
ምንድነው ፡ መጨነቅ ፡ ምንድነው ፡ መሸበር
እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ሁሉን ፡ የሚችለው
ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ማዘነሽ ፡ ከቶ ፡ ለምንድን ፡ ነው

አዝ፦ ነፍሴ ፡ አታስጨንቂኝ
እስቲ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ታመኚ (፪x)

እስኪ ፡ ያለፍሽበትን ፡ ጐዳና
ኣንቺ ፡ መለስ ፡ ብልሽ ፡ እይና
ጌታ ፡ ከምን ፡ ከምን ፡ አዳንሽ
እንዴት ፡ እንዴት ፡ አርጐስ ፡ ታደገሽ (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ አታስጨንቂኝ
እስቲ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ታመኚ (፪x)

ጌታ ፡ ምህረቱን ፡ ዘጋ ፡ ወይ
ይሄ ፡ ስንፈናዬ ፡ አይደል ፡ ወይ
እርሱ ፡ ቢዘገየም ፡ ይመጣል
ሁሉን ፡ አዲስ ፡ አዲስ ፡ ያደርጋል

ፊትህን ፡ ወደኔ ፡ ከመለስክልኝ
አንተን ፡ ደስ ፡ ካለህ ፡ ካልተቆጣኸኝ (፪x)
ዓይኖችህ ፡ ካዩኝ ፡ ጆሮህን ፡ ከሰማኝ
ይሄ ፡ ይበቃኛል ፡ እረካለሁኝ (፪x)

አለኝ ፡ ይምለው
ተስፋ ፡ ማደርገው ፡ የምመካበት
መገኘትህ ፡ ብቻ ፡ ነው
ፊትህን ፡ ብቻ ፡ ነው
መገኘትህ ፡ ብቻ ፡ ነው
ፍቅርህን ፡ ብቻ ፡ ነው

አለኝ ፡ ይምለው
ተስፋ ፡ ማደርገው ፡ የምመካበት
ፍቅርህን ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ህልውናህ ፡ ብቻ ፡ ነው
መገኘትህ ፡ ብቻ ፡ ነው