Thursday, February 16, 2017

የእኔማ Yeniema የእኔማ የእኔማ ሰላም የእኔማ

አውታሩ  ከበደ

የእኔማ ፣ የእኔማ ፡ ሰላም ፡ የእኔማ
የእኔማ ፣ የእኔማ ፡ ደስታ ፡ የእኔማ (፪x)

ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አይደለም ፡ በመንፈሱ ፡ ነው
በብርም ፡ በወርቅም ፡ የማይገዛው
በወንጌል ፡ ሞኝነት ፡ በአመንኩት ፡ ቃል
ሰላሙ ፡ ከሆዴ ፡ ይፍለቀለቃል

አገዘኝ ፡ አገዘኝ (፰x)

ጠላቴ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
በመንፈሱ ፡ ነካኝ ፡ አትረፈረፈኝ
አገር ፡ ምድሩ ፡ እያየ
በቅባቱ ፡ ነካኝ ፡ አትረፈረፈኝ

አገዘኝ ፡ አገዘኝ (፰x)

ላምልክህ ፡ ደግሜ ፡ እስኪ ፡ ደግሜ ፡ ደጋግሜ (አሄ)
ላምልክህ ፡ ደግሜ ፡ እስኪ ፡ ደግሜ ፡ ደጋግሜ (፪x)

ይውጣ ፡ ወደላይ ፡ ከድንኳኔ
የአምልኮ ፡ የዝማሬው ፡ ቅኔ
የሆንክልኝን ፡ ሳስበው
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ምሆነው

ከፍ ፡ በልልኝ (፬x)
ደምቀህ ፡ ታይልኝ (፬x)

ና ፡ ሲለኝ ፡ ቃሉን ፡ ተማምኖ ፡ በውኃው ፡ ላይ
ና ፡ ሲለኝ ፡ እጁ፡ እንደማይጥል ፡ አታዩም ፡ ወይ
ና ፡ ሲለኝ ፡ ከሁኔታ ፡ ጋር ፡ እርሱ ፡ አይለካ
ና ፡ ሲለኝ ፡ መንገድ ፡ ይሆናል ፡ ውኃውም ፡ ለካ

ጠላቴ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
በመንፈሱ ፡ ነካኝ ፡ አትረፈረፈኝ
አገር ፡ ምድሩ ፡ እያየ
በእሳቱ ፡ ነካኝ ፡ አትረፈረፈኝ

አገዘኝ ፡ አገዘኝ (፰x)

የእኔማ ፡ የእኔማ ፡ ሰላም ፡ የእኔማ
የእኔማ ፡ የእኔማ ፡ ደስታ ፡ የእኔማ (፪x)

ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አይደለም ፡ በመንፈሱ ፡ ነው
በብርም ፡ በወርቅም ፡ የማይገዛው
በወንጌል ፡ ሞኝነት ፡ በአመንኩት ፡ ቃል
ሰላሙ ፡ ከሆዴ ፡ ይፍለቀለቃል

አገዘኝ ፡ አገዘኝ (፰x)

ላምልክህ ፡ ደግሜ ፡ እስኪ ፡ ደግሜ ፡ ደጋግሜ (አሄ)
ላምልክህ ፡ ደግሜ ፡ እስኪ ፡ ደግሜ ፡ ደጋግሜ (፪x)

ይውጣ ፡ ወደላይ ፡ ከድንኳኔ
የአምልኮ ፡ የዝማሬው ፡ ቅኔ
የሆንክልኝን ፡ ሳስበው
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ምሆነው

ከፍ ፡ በልልኝ (፬x)
ደምቀህ ፡ ታይልኝ (፬x)