Tuesday, August 16, 2016

እኔ የማምነው Enie Yemamnew አዲስዓለም አሰፋ Addisalem Assefa #2

አዲስዓለም አሰፋ Addisalem Assefa 
በዙሪያዬ ፡ ያለው ፡ ነገሬ ፡ ይህን ፡ ባይነግሬኝ
ነገርሽ ፡ ሞተ ፡ ተቀበረ ፡ በቃ ፡ ብለኝ
አዲስ ፡ ነገር ፡ ማድረግ ፡ ሁልጊዜ ፡ ልማድ ፡ ያለው ፡ ጌታ
ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ይተጋል ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ከፍታ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ የማምነው ፡ ጨለማሽ ፡ ይበራል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ የማምነው ፡ ተራራሽ ፡ ይናዳል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)

አላምንም ፡ ሁኔታን ፡ አላምንም ፡ ችግሬን
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይሰራል ፡ ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይከፍታል ፡ መቃብሬን (፪x)

ልቤን ፡ ልጣል ፡ እንጂ ፡ በሚያስጥለው ፡ ጌታ
በእርሱ ፡ ተደግፌ ፡ ጉልበቴን ፡ ላበርታ
ታምራት ፡ ያሳየኛል ፡ ጌታ (፬x)

በደረቁ ፡ አጥንቶች ፡ ነፍስን ፡ መዝራት
እንደ ፡ ሰው ፡ ሲታሰብ ፡ በምን ፡ ጉልበት
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ቀላል ፡ ነው
እጁ ፡ ድንቅ ፡ ይሰራል ፡ ትልቅ ፡ ነው

ልጅ ፡ መውለድ ፡ በዘጠና ፡ ዓመት
ለሣራ ፡ ከባድ ፡ ነው ፡ ሲገመት
ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ካለ ፡ ሆነ ፡ ነው
ታምር ፡ የሚሰራ ፡ ጌታ ፡ ነው [1]

እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
ኧረ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
ያልታሰበ ፡ ነገር ፡ ያደርጋል ፡ በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ የማምነው ፡ ጨለማሽ ፡ ይበራል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ የማምነው ፡ ተራራሽ ፡ ይናዳል ፡ ያለኝን ፡ ነው (፪x)

አላምንም ፡ ሁኔታን ፡ አላምንም ፡ ችግሬን
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይሰራል ፡ ነገሬን (፪x)
እግዚአብሔርን ፡ አምነዋለሁ ፡ ይከፍታል ፡ መቃብሬን (፪x)

ልቤን ፡ ልጣል ፡ እንጂ ፡ በሚያስጥለው ፡ ጌታ
በእርሱ ፡ ተደግፌ ፡ ጉልበቴን ፡ ላበርታ
ታምራት ፡ ያሳየኛል ፡ ጌታ (፬x)