Tuesday, February 23, 2016

ባለፍኩበት መንገድ

 ተስፋዬ  ጋቢሶ  Tesfaye Gabiso

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ (፪x)

ማዕበሉ ፡ ሳይጥለኝ ፣ ውኃ ፡ ሳያሰጥመኝ
እጄን ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ወንዝ ፡ አሻገረኝ
የፈተናው ፡ እሣት ፡ ወላፈን ፡ ሳይጐዳኝ
በጌታዬ ፡ ፀጋ ፡ በሕይወት ፡ አለፍኩኝ

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ (፪x)

ከሕያዋን ፡ ጋራ ፡ ኖሬ ፡ እንዳከብርህ
ፈተናን ፡ አልፌ ፡ እንዳመሰግንህ
ኢየሱስ ፡ ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ አበረታኝ
ከአንበሣው ፡ አፍም ፡ ደጋግሞ ፡ አወጣኝ




አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ (፪x)

ሕይወቴን ፡ ለአምላኬ ፡ አደራ ፡ እየሰጠሁ
በእረኝነቱ ፡ ሥር ፡ ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
በእርሱ ፡ ተጠብቄ ፡ አገሬ ፡ እገባለሁ

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ (፪x)

ጌታ ፡ የሠራውን ፡ ድንቅ ፡ አስታውሳለሁ
ስላለፈው ፡ ዘመን ፡ አመሰግናለሁ
ከፊቴ ፡ ላለውም ፡ በእርሱ ፡ እደገፋለሁ
በዘለዓለም ፡ ክንዱ ፡ በእቅፉ ፡ እኖራለሁ

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ (፪x)
Download Lyrics