Monday, February 29, 2016

ነው ወይስ ይህ ዘመን ቁጥር የማይዘመርበት ነው??????












ይህንን ጦማር (Blog) ለመጀመር ያነሳሳ ዋናው ነገር አሁን በብዙ ቤተክርስቲያኖች ያለው የዝማሬ አምልኮ አካሄድ ነው፡፡ ይህም ብዙ የተለያዩ መዝሙሮች አዝማች ብቻ እየተቀጣጠለ ቁጥሮች የማይዘመሩበት ሲሆን ይህም በከፍተኛ ሁኔታ እየተለመደ የመጣ መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዴ  ሲብስ ደግሞ ጭራሽ በመልእክትም ሆነ በሀሳብ አብረው የማይሄዱ የተለያዩ መዝሙሮች አዝማች፤ ሪትማቸው ወይም የሙዚቃ ስልተ ምታቸው ተመሳሳይ ስለሁነ ብቻ ተቀጣጥለው ይዘመራሉ፡፡ በርግጥ ይህ ነገር ከሁላችሁም አይን የተሰወረ አይመስለኝም፡፡ ይህም ደግሞ ሙሉ የመዝሙሮቹን ሀሳብ እንዳንረዳ እና ጥልቅ ወደሆነ የአምልኮ መንፈስ ውስጥ እንዳንገባ ያደርገናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ፡ አንድ ስለ እየሱስ የመስቀል ፍቅር የሚናገር መዝሙር አየዘመርን ሌላ እግዚአብሔር በምድር ስለ ሰጠን ስኬት የሚያወሳ መዝሙር ቢቀጠልበት ፤ የመጀመሪያውን መዝሙር ቀጥሮች ብንዘምር ስለ መስቀሉ ይበልጥ እንድናስብ ያደርገናል ይህም ጥልቅ ወደሆነ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ምስጋና እንድናቀርብ ያስችለናል፡፡ በተቃራኒው ቁጥሮቹ ተትተው ከላይ የገለጽኩት መዝሙር ሲቀጠል ግን ምስጋናችን ጥልቀቱ ቀንሶ በምድር ስለተደረገልን ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እናንተም ሌሎች ብዙ ምሳሌዎች መጨመር ትችላላችሁ፡፡ ነው ወይስ ይህ ዘመን ቁጥር የማይዘመርበት ነው??????

Holymezmur Lyrics