Monday, February 29, 2016

አቤቱ ጉልበቴ ሆይ Abetu Gulbte Hoy Ewdehalw


 
Lily Tilahun

                ሊሊ ጥላሁን Lily Tilahun 


 አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ
አቤቱ የኔ ጌታ እወድሃለሁ
እግዚአብሔር አለቴ አንባ መድኃኒቴ
የምታመንበት ሆነኝ ረዳቴ /2

በዙሪያዬ ሆኖ ጠላት ሲያውከኝ
ያሸነፈኝ መስሎት ሲፎክርብኝ
በጨነቀኝ ጊዜ ወዳንተ ጮኽኩኝ
ሰማይን ዝቅ አድርገህ ከተፍ አልክልኝ

እጆቼን አንስቼ ተገፋሁ አልኩኝ
እግዚአብሔር ከሰማይ ተበቀለልኝ
ምድር ተናወጠች ቁጣውም ነደደ
በጠላቶቼ ላይ መብረቅ አወረደ

እግሮቼም ቆሙልኝ አልተንሸራተቱም
ጠላቶቼን ያዝኩኝ አላመለጡኝም
በኮረብቶችም ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ
እስቲ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ

ለሚታመኑበት እርሱ ጋሻ ነው
ክፉዬን አይወድም ይነዳል ቁጣው
ከመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ይሰማኛል
እግዚአብሔርን አይቶ ጠላቴ ፈርቶኛል