ዮሴፍ በቀለ Yosef Bekele
በረጅምና ፡ ከፍ ፡ ባለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ለተቀመጥከው (፪x)
ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ ይኸው ፡ ይዤ ፡ መጣሁ ፡ ለአንተ ፡ ልሰዋ (፪x) ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩኝ ፡ ወደ ፡ ማደሪያህ ፡ እገባለሁኝ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩኝ ፡ ወደ ፡ መቅደስህ ፡ እገባለሁኝ አዝ፦ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x) ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x) ቅዱስ ፡ እያሉህ ፡ ሲያመልኩ ፡ መላዕክቱ ክብርህ ፡ ቤቱን ፡ ሞልቶት ፡ ነበር ፡ ኦ ፡ አቤቱ እኔም ፡ ከልቤ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩ ፡ እጮሃለሁ አንተ ፡ ቅዱስ ፡ መሆንህን ፡ አውጃለሁ አዝ፦ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x) አመልካሃለሁ ፡ ቅዱስ ፡ እያልኩኝ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ስላላየሁኝ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x) ለዘለዓለም ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ተቀምጠሃል ደፍሮ ፡ ከዙፋንህ ፡ ና ፡ ውረድ ፡ ማን ፡ ይልሃል አይቆጠርም ፡ ዘመናትህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ቅዱስ ፡ እያልኩኝ ፡ ልስገድልህ ፡ በዕልልታ አዝ፦ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x) ይደርደርልህ ፡ ዛሬም ፡ በገናው በዕልልታ ፡ ሆታ ፡ ቅኔ ፡ ምሥጋናው ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x) ስራህ ፡ ትክክል ፡ እውነተኛ ፡ እንከን ፡ የለህ ነውር ፡ ነቀፋ ፡ የሌለብህ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፍርድ ፡ አታጓድል ፡ አታደላ ፡ ጻድቅ ፡ አምላክ ነፍሴ ፡ ሁልጊዜ ፡ በምሥጋና ፡ አንተን ፡ ትበል አዝ፦ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (፬x) የጌታዎች ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ የአማልክት ፡ አምላክ ፡ አምላክ ፡ አምላክ ፡ የእስራኤል ፡ ቅዱስ ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ስምህ ፡ ይወደስ ስምህ ፡ ይቀደስ ፡ ዛሬም ፡ ልዘለዓለም ይወደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x) ይቀደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x) ይወደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x) ይቀደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x) ይወደስ ፡ ክቡር ፡ ስምህ (፪x) |