Monday, August 8, 2016

ባለውለታዬ Balewuletayie ተፈራ ነጋሽ

ተፈራ ነጋሽ Tefera Negash

እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አድነኸኛል
አመልክሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤዛ ፡ ሆነኸኛል
አመሰግናለሁ ፡ ጌታ ፡ ታድገኸኛል
አከብርሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ አድርገኸኛል

ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ
ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ
ይሄ ፡ ብቻ ፡ አይበቃህም ፡ ጌታ

ከሞት ፡ መንደር ፡ በምህረትህ ፡ በቸርነትህ ፡ አውጥተህ
ጨለማውን ፡ አስወግደህ ፡ ለዚህ ፡ ክብር ፡ ያበቃኸኝ
ሳትሰለች ፡ እያባበልክ ፡ ከኃጢአት ፡ በደሌን ፡ ታግሰህ
ሰው ፡ አረግከኝ ፡ አተረፍከኝ ፡ ነፍሴን ፡ ከጥፋት ፡ መልሰህ

አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ
ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x)

ያለ ፡ እረኛ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ በዓለም ፡ ወጥመድ ፡ ተይዤ
ፈጣሪዬን ፡ ስበድል ፡ ሳሳዝን ፡ በክፉ ፡ ደንዝዤ
እራራህልኝ ፡ ደረስክልኝ ፡ ጸያፍ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው
ልጅ ፡ ተባልኩኝ ፡ ክብር ፡ አገኘሁ ፡ ስሜን ፡ በደም ፡ ቀለም ፡ ጻፍከው

አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ
ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x)