Monday, August 8, 2016

ዕድሜዬ በቤትህ ይለቅ Edmieyie Bebieteh Yileq ቤተልሔም ተዘራ

ቤተልሔም ተዘራ Bethlehem Tezera
ቤትህን ፡ ሊሰራ ፡ የተመረጠው
የተወደደ ፡ ጥበብ ፡ የሞላው (፪x)
ክብር ፡ ሲሆንልት ፡ ዝና ፡ ሲተርፈው
የአባቶቹን ፡ አምላክ ፡ እንደማያውቀው
ጣዖት ፡ አምልኮ ፡ ሞት ፡ ሆነ ፡ ፍጻሜው

አዝ፦ ዕድሜዬ ፡ ይለቅልኝ ፡ ቤትህ
ይለቅልኝ ፡ በፊትህ
ሕይወቴ ፡ ይመርልኝ ፡ ፊትህ
ይመርልኝ ፡ በፊትህ

ሩጫዬ ፡ እንዳይገታ
ጠብቀኛ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እኔ ፡ እንዳልሆን ፡ ለእኔው ፡ ጠላቴ
ሰውረኝ ፡ ከዓይን ፡ አምሮቴ (፪x)

አህያ ፡ ፍለጋ ፡ ተልኮ ፡ ቢወጣ
እጣ ፡ ወደቀበት ፡ ህዝብን ፡ እንዲመራ
ከፍልስጤማዊ ፡ ነጻ ፡ እንዲያወጣ

ደርሶ ፡ ንጉሥ ፡ ሲሆን ፡ ትህትና ፡ አጣ
ክፉ ፡ መንፈስ ፡ ያዘው ፡ ከአንተ ፡ መንገድ ፡ ወጣ
መውደቂያው ፡ ሆነበት ፡ የጊልቦዓ ፡ ተራራ

አዝ፦ ዘመኔ ፡ ይለቅልኝ ፡ ቤትህ
ይለቅልኝ ፡ በፊትህ
ሕይወቴ ፡ ይመርልኝ ፡ ፊትህ
ይመርልኝ ፡ በፊትህ

ሩጫዬ ፡ እንዳይገታ
ጠብቀኛ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እኔ ፡ እንዳልሆን ፡ ለእኔው ፡ ጠላቴ
ሰውረኝ ፡ ከዓይን ፡ አምሮቴ (፪x)

በትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ ዓይናቸው ፡ የበራ
ጨከኑ ፡ በሕይወት ፡ ለሰሙት ፡ አደራ
ቤታቸውን ፡ ሰጡ ፡ ለወንጌል ፡ አደራ

አርበኞች ፡ ሆነዋል ፡ እስሩም ፡ ቢጠና
ነገሥታት ፡ ፊት ፡ ቆሙ ፡ ወንጌልን ፡ ሰበኩና
ሳማአት፡ ሆነው ፡ አለፉ ፡ ዋጋ ፡ ተመኑና

ድል ፡ ለነሳው ፡ ከሕይወት ፡ አክሊል ፡ ታቀዳጃለህ
ድል ፡ ለነሳው ፡ በቤትህ ፡ እንዲኖር ፡ ትሾመዋለህ
ጅማሬዬ ፡ እንዳማረልኝ ፡ ፍጻሜዬም ፡ ይስመርልኝ
መዝገብ ፡ ላከማች ፡ በሠማይ ፡ ቤትህ
ብል ፡ በማይበላው ፡ በሌለበት

ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዕድሜዬ ፡ ይልቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዘመኔ ፡ ይልቅ ፡ እቤትህ (፪x)

ድል ፡ ለነሳው ፡ ከሕይወት ፡ አክሊል ፡ ታቀዳጃለህ
ድል ፡ ለነሳው ፡ በቤትህ ፡ እንዲኖር ፡ ትሾመዋለህ
ጅማሬዬ ፡ እንዳማረልኝ ፡ ፍጻሜዬም ፡ ይስመርልኝ
መዝገብ ፡ ላከማች ፡ በሠማይ ፡ ቤትህ
ብል ፡ በማይበላው ፡ በሌለበት

ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዕድሜዬ ፡ ይልቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዘመኔ ፡ ይልቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ሕይወቴ ፡ ይመር ፡ እፊትህ

ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ወበቴ ፡ ይልቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዕድሜዬ ፡ ይልቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዘመኔ ፡ ይልቅ ፡ እቤትህ