Tuesday, August 16, 2016

እግዚአብሔር ሲናገር Egziabhier Sinager አውታሩ ከበደ Awtaru Kebede #5

አውታሩ  ከበደ Awtaru Kebede
እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ሁሉንም ፡ ይችላል ፡ እኔ ፡ ዝም ፡ ልበል
አምላኬ ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ኃይል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ምድር ፡ ዝም ፡ ትበል

ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)

ሞቷል ፡ አይ ፡ ቀበርከው ፡ አይ
ዛሬ ፡ ቀኑ ፡ ነው (፫x) ፡ ክብሩን ፡ ልታይ
ቀኑ ፡ ነው ፡ ክብሩን ፡ ልታይ (፬x)

አረጀ ፡ አብርሃም ፡ ደከመ ፡ ጉልበቱ
ዛሬማ ፡ አይደለም ፡ እንደ ፡ ልጅነቱ
አበቃ ፡ ተቁርጧል ፡ የእርሱ ፡ ነገርማ
ምድር ፡ ተገረመች ፡ መውለዱ ፡ ሳይሰማ
ምንም ፡ በሌለበት ፡ ጭር ፡ ባለው ፡ ቦታ
አድሞ ፡ ጀመረ ፡ ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ ጌታ

ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)

ብቻ ፡ ይናገረኝ ፡ ቃሉን ፡ . (1) .
እጠብቀዋለሁ ፡ ቀኑ ፡ ቢሆን ፡ ክፉ
በገናን ፡ አልሰቅልም ፡ እደረድራለሁ
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አባቴ ፡ ትልቅ ፡ ነው
አባቴ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
በእርሱ ፡ ለታመኑ/ታምኛለሁ ፡ ይፈርዳል ፡ ከሰማይ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ሁሉንም ፡ ይችላል ፡ እኔ ፡ ዝም ፡ ልበል
አምላኬ ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ኃይል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ምድር ፡ ዝም ፡ ትበል

ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)

ሞቷል ፡ አይ ፡ ቀበርከው ፡ አይ
ዛሬ ፡ ቀኑ ፡ ነው (፫x) ፡ ክብሩን ፡ ልታይ
ቀኑ ፡ ነው ፡ ክብሩን ፡ ልታይ (፬x)

የማሰሮው ፡ ዘይት ፡ የማድጋው ፡ ዱቄት
አንድ ፡ ቀን ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ነገ ፡ የለም ፡ ሕይወት
እያለች ፡ ተጨንቃ ፡ ከአንድ ፡ ልጇ ፡ ጋራ
እግዚአብሔር ፡ አሰባት ፡ መጣ ፡ የእርሷ ፡ ተራ
ዝናብ ፡ እስኪመጣ ፡ ምድር ፡ እስኪያበቅል
በበረከት ፡ ሞላው ፡ ቤቷን ፡ በሰላም

ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)