አገኘሁ ይደግ Agegnehu Yideg
በግብፃውያን ፡ መንደር ፡ ጨለማው ፡ በርክቷል
በእኔ ፡ ቤት ፡ ብርሃኔ ፡ ኢየሱሴ ፡ በርቷል የጠላቴን ፡ መንገድ ፡ ሁካታ ፡ ሞልቶታል የእኔ ፡ ግን ፡ ድንኳኔ ፡ በዕልልታ ፡ ተሞልቷል አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x) ሲሳካም ፡ ዕልልታ ሳይሆንም ፡ ዕልልታ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ ተራራም ፡ ዕልልታ ሸለቆም ፡ ዕልልታ አቀዋለሁ ፡ ጌታ አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x) እያልኩኝ ፡ ብውል ፡ ባድር አይገልጥም ፡ የአንተን ፡ ክብር እያልኩኝ ፡ በበገናዬ ማደሪያህ ፡ ልግባ ፡ ጌታዬ አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x) ጳውሎስና ፡ ሲላስ ፡ እስር ፡ ቤት ፡ ሆነው የመጣህላቸው ፡ ሲዘምሩ ፡ ነው የውህኒው ፡ መሠረት ፡ የተናወጠው ሲቆዝሙ ፡ አይደለም ፡ በዕልልታ ፡ እኮ ፡ ነው አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x) ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ የሚያዘምረኝ ተቆጥሮ ፡ የማያልቅ ፡ ውለታ ፡ አለብኝ ፡ ኦ ዘሬ ፡ ቢገዛለት ፡ ፍጥረትም ፡ ቢያመልከው የእርሱን ፡ ህልውና ፡ ማነው ፡ የሚተርከው በበጋም ፡ ዕልልታ በክረምት ፡ ዕልልታ አትለወጥ ፡ ጌታ ሲዘጋም ፡ ዕልልታ ሲከፈት ፡ ዕልልታ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x) እያልኩኝ ፡ ብውል ፡ ባድር አይገልጥም ፡ የአንተን ፡ ክብር እያልኩኝ ፡ በበገናዬ ማደሪያህ ፡ ልግባ ፡ ጌታዬ አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፬x) ግርማውና ፡ ክብሩ ፡ ፊቱ ፡ ይታየኛል ነፍስም ፡ አልቀረልኝ ፡ ዕልልታ ፡ ሞልቶኛል (እሰይ ፡ የእኔ ፡ ጌታ) ከበሮ ፡ ይመታ ፡ ይደርደር ፡ በገና ከጥንት ፡ ለዘለዓለም ፡ ብቻውን ፡ ገናና አዝ፦ ዕልልታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ (፲፪x) |