Tuesday, August 9, 2016

ከቁጥር በዛ Kequter Beza ተመስገን ማርቆስ Temesgen Markos #1

ተመስገን ማርቆስ Temesgen Markos


አዝ፦ እንዴት ፡ ተደርጐ ፡ ይወራል
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ አባባ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ (፪x)

ስራህ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው
ባወራው ፡ ብናገር ፡ አልጨርሰው
ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ እጅግ ፡ ብዙ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላውራው ፡ ስራህ ፡ ብዙ (፫x)

አዝ፦ እንዴት ፡ ተደርጐ ፡ ይወራል
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ አባባ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ

የተደረገልኝ ፡ የሆነልኝ
ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የሰራልኝ
ብዙ ፡ ተደርጐልኝ ፡ አይቻለሁ
ልናገረው ፡ ቃላት ፡ አጥቻለው
እንዲያው ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ

አዝ፦ እንዴት ፡ ተደርጐ ፡ ይወራል
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ አባባ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ

አንደበቴን ፡ ልክፈት ፡ ልናገረው
ላሰማ ፡ ስራህን ፡ ልተርከው
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ስራ
እንዴትስ ፡ አድርጌ ፡ እንዴት ፡ ላውራ
አስገረመኝ ፡ የአንተ ፡ ስራ

አዝ፦ እንዴት ፡ ተደርጐ ፡ ይወራል
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ ጌታዬ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ ፡ አባባ
ከቁጥር ፡ በዛ ፡ ስራህ (፪x)