Friday, August 5, 2016

ማስረሺያዬ Masreshiyayie ቃለአብ ፀጋዬ Kaleab Tsegaye

ቃለአብ  ፀጋዬ Kaleab Tsegaye


ሃዘኔን ፡ የረሳሁብህ
ይዤህ ፡ ወጥቼ ፡ ያላፈርኩብህ
ለቅሶዬን ፡ የረሳሁብህ
ይዤህ ፡ ወጥቼ ፡ ያላፈርኩብህ

አዝ:- ማስረሺያዬ (፫x) ፡ ማስረሺያዬ (፫x)
ማስረሺያዬ (፬x)

እናት ፡ ከእናትም ፡ በላይ ፡ ነው
አባት ፡ ከአባትም ፡ በላይ ፡ ነው
ማን ፡ ልበለው ፡ ኧረ ፡ ማን (፪x)
ኧረ ፡ ማን ፡ ልበለው ፡ ኧረ ፡ ማን (፪x)

ወንድም ፡ ጋሼ ፡ አልኩት
መከታዬ ፡ አልኩት
ተመቸኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ

ሳለቅስ ፡ የደረሰ ፡ እንባዬን ፡ የአበሰ
ሰዎች ፡ ሲርቁኝ ፡ እኔ ፡ አለሁልህ ፡ ያለኝ
ጉድጓዱን ፡ አሻገረኝ (፪x)

ከመንገድ ፡ ላይ ፡ አነሳኀኝ
ያለእድሜዬ ፡ አከበርከኝ ፡ ሰው ፡ አደረከኝ
ከትልልቅ ፡ ሰዎች ፡ ጋራ ፡ አደባለከኝ (፪x)

እድሜዬ ፡ አይፈቅድልኝ ፡ ጊዜም ፡ አይፈቅድልኝ
ሁኔታው ፡ አይፈቅድልኝ ፡ ዕውቀቴ ፡ አይፈቅድልኝ

ሰው ፡ ያደረከኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሰው ፡ ያደረከኝ (፬x)

እድሜዬ ፡ አይፈቅድልኝ ፡ ጊዜም ፡ አይፈቅድልኝ
ሁኔታው ፡ አይፈቅድልኝ ፡ ዕውቀቴ ፡ አይፈቅድልኝ

ምን ፡ እላለሁ ፡ ምን ፡ እላለሁ
አመሰግናለሁ (፪x)