Friday, August 5, 2016

ደሙ Demu ምህረት ኢተፋ Meheret Etefa

ምህረት ኢተፋ Meheret Etefa

በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ
ክብሬ (፯x)
ሞገሴ

ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር
የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ
የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ
 (፪x)
ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ
ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ

የሞት ፡ መልአክት ፡ አያስፈራኝ
ተሸፍኛለሁ ፡ አያገኘኝ (፪x)
ዙሪያዬ ፡ ከደሙ ፡ ታጥሯል
ያን ፡ ቅጥር ፡ አልፎ ፡ እንዴት ፡ ይገባል (፪x)

ለጠላቴ ፡ የሃዘን ፡ ለእኔ ፡ የደስታ ፡ ቀን ፡ ነው
ሞት ፡ እየገባ ፡ ያለው ፡ በጠላቴ ፡ መንደር ፡ ነው
ይዙር ፡ እንጂ ፡ ዙሪያዬን ፡ እንደሚያገሳ ፡ አንበሳ
ፍፁም ፡ አይቀናም ፡ አይችልም ፡ ከደሙ ፡ የተነሳ
 (፪x)

ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላንስህ ፡ ለተገባው
ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላንስህ ፡ ለተገባው
ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር
የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ
የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ
 (፪x)
ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ
ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ

በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ
ክብሬ (፯x)
ሞገሴ