ተከስተ ጌትነት Tekeste Getnet
መቼ ፡ ዘነጋሁት ፡ የትላንቱን ፡ ነገር
ከሞት ፡ የመትረፌ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር በአደባባይ ፡ ልቁም ፡ የአረከውን ፡ ላውራ የት ፡ እደርስ ፡ ነበረ ፡ ባልሆን ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) አዝ፦ ትላንትን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ከጨካኙ ፡ ከአውሬው ፡ ተርፌ ሳልሰጋ ፡ ልኑር ፡ በደጅህ ለዛሬም ፡ ትምክቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፪x) ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ለእኔ ፡ የለም (፫x) ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ለእኔ ፡ የለም (፫x) የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላ ፡ ከልለህ ድቅድቁን ፡ ጨለማ ፡ በብርሃን ፡ ለውጠህ ቁር ፡ ሳያገኘኝ ፡ እባቡ ፡ ሳይነድፈኝ አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ከስንቱ ፡ ታደከኝ (፪x) አዝ፦ ትላንትን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ከጨካኙ ፡ ከአውሬው ፡ ተርፌ ሳልሰጋ ፡ ልኑር ፡ በደጅህ ለዛሬም ፡ ትምክቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፪x) ትዝ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያረክልኝ ፡ ሁሉ ሳልቆጥብ ፡ ልናገር ፡ ዘመኔን ፡ በሙሉ ጌታ ፡ ማዳንህን ፡ ለሰው ፡ ሳላወራ አንድም ፡ ቀን ፡ አያልፍም ፡ ስምህን ፡ ሳልጠራ (፪x) አዝ፦ ትላንትን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ከጨካኙ ፡ ከአውሬው ፡ ተርፌ ሳልሰጋ ፡ ልኑር ፡ በደጅህ ለዛሬም ፡ ትምክቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፪x) |