Tuesday, August 9, 2016

ወደድከኝ Wededkegn ቴዎድሮስ ታደሰ Teodros Tadesse

ቴዎድሮስ ታደሰ Teodros Tadesse

ወደድከኝ(፫x) ፡ እንዲያው ፡ ወደድከኝ
ወደድከኝ(፫x) ፡ የፍቅር ፡ ነህ ፡ እንዲያው ፡ ወደድከኝ

ታዛዥ ፡ አልነበርኩም ፡ አመጸና ፡ እንቢተኛ
እንደልቤ ፡ ምኖር ፡ ዓለም ፡ ወዳድ ፡ ዓለመኛ
ፍቅርህ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ወደውስጤ ፡ ዘልቆ ፡ ገባ
ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ ሰበሰበኝ ፡ እንድልህ ፡ አባ

አባ ፡ ልበል ፡ ከወደድከኝ ፣ አባ ፡ ልበል ፡ ከመረጥከኝ
አባ ፡ ልበል ፡ በቸርነትህ ፣ አባ ፡ ልበል ፡ ከደገፍከኝ
አባ ፡ ልበል ፡ ልስገድልህ ፣ አባ ፡ ልበል ፡ ልቀኝልህ
አባ ፡ ልበል ፡ እንዳየህልኝ ፣ አባ ፡ ልበል ፡ ልኑርልህ
አባብዬ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ እድል ፡ ፈንታዬ
አብትዬ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ እድል ፡ ፈንታዬ
ወደድከኝ(፫x) ፡ እንዲያው ፡ ወደድከኝ
ወደድከኝ(፫x) ፡ የፍቅር ፡ ነህ ፡ እንዲያው ፡ ወደድከኝ

ሰዎች ፡ የናቁትን ፡ የገፉትን ፡ የረሱትን ፡ ሰው
ሰው ፡ አይሆንም ፡ ብለው ፡ የተዉትን ፡ አንተ ፡ ታደከው
ዛሬ ፡ በአደባባይ ፡ ይዘምራል ፡ ተቀብቶ
የአለፈው ፡ ታሪኩ ፡ እንዳለፈ ፡ ዉሃ ፡ ተረስቶ

ምን ፡ ይባላል ፡ ተመስገን ፡ እንጂ
ምን ፡ ይባላል ፡ አንተ ፡ ስትረዳ
ምን ፡ ይባላል ፡ ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ
ምን ፡ ይባላል ፡ የማትከዳ (፪x)
አባብዬ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ እድል ፡ ፈንታዬ
አብትዬ (፪x) ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ እድል ፡ ፈንታዬ