Friday, August 5, 2016

ትንሳዔውን ተናገሩ Tensaewen Tenageru

                           ሄኖክ አዲስ Henok Addis

                           


አብቃለት ፡ ተብሎ ፡ ነበር ፡ ኢየሱስ ፡ ሰቀበር
ወሬ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር
አለፈ ፡ ተብሎ ፡ ቢወራ ፡ ነበር ፡ ተብሎ ፡ ሊዘከር
ወሬ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር
የዓለምን ፡ ታሪክ ፡ ለወጠ ፡ ነገር ፡ ተገለበጠ
ያ ፡ . (1) . ፡ አመለጠ
መቃብሩን ፡ ፈነቃቅሎ ፡ ሰይጣንን ፡ ጉድ ፡ አረገ
ወደ ፡ አባቱ ፡ አረገ

የሰማ ፡ ያልተወገደ ፡ ተሻረ ፡ የእኛ ፡ አበሳ
በትንሳዔ ፡ ድል ፡ ነሳ
መቼ ፡ እንደሞተ ፡ ቀረ ፡ ከሙታንም ፡ ተነሳ
በትንሳዔው ፡ ድል ፡ ነሳ

ኢየሱስ ፡ ተነሳ
ጌታዬ ፡ ተነሳ (፪x)

ትንሳዔውን ፡ ተናገሩ ፡ የእምነት ፡ አባቶች ፡ መሰከሩ
እኔም ፡ ለትውልድ ፡ ልናገርው
ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ ልመስክረው (፪x)

ተነስቷል ፡ ይሄ ፡ ጌታ
ማኅተሙን ፡ እርሱ ፡ ፈታ
ቅዱሳን ፡ በአንድ ፡ ኑና
አክብሩት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ዕልልታ ፡ ሙገሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቷል ፡ አክብሩት ፡ ቅዱሳን
የታል ፡ ዕልልታ ፡ ለዓለሙ ፡ ጌታ
የታል ፡ ጭብጨባ ፡ መቅደሱ ፡ የሚገባ (፪x)

ኃይል ፡ እንደሌለው ፡ ቢመታ ፡ ወደ ፡ መስቀል ፡ ቢነዳ
በትንሳዔው ፡ ደል ፡ ነሳ
በእንጨት ፡ ላይ ፡ ቢንጠለጠል ፡ ስለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ቢጐዳ
በትንሳዔው ፡ ደል ፡ ነሳ
ቢያሾፉ ፡ ቢያሳልቁበት ፡ እያሙ ፡ በበረዳ
በትንሳዔው ፡ ደል ፡ ነሳ
በደሙ ፡ እርቅ ፡ አወረደ ፡ አፈረሰ ፡ ያን ፡ ግድግዳ
በትንሳዔው ፡ ደል ፡ ነሳ

ትንሳዔውን ፡ ተናገሩ ፡ የእምነት ፡ አባቶች ፡ መሰከሩ
እኔም ፡ ለትውልድ ፡ ልናገርው
ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ ልመስክረው (፪x)

ተነስቷል ፡ ይሄ ፡ ጌታ
ማኅተሙን ፡ እርሱ ፡ ፈታ
ቅዱሳን ፡ በአንድ ፡ ኑና
አክብሩት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ዕልልታ ፡ ሙገሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቷል ፡ አክብሩት ፡ ቅዱሳን
የታል ፡ ዕልልታ ፡ ለዓለሙ ፡ ጌታ
የታል ፡ ጭብጨባ ፡ መቅደሱ ፡ የሚገባ (፪x)