Friday, August 5, 2016

ተመችቶኝ ነው Temechetogn New

መስከረም ጌቱ Meskerem Getu


አዝ፦ ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ ተመችቶኝ ፡ ነው (፬x)
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፬x)

ሲከፋኝ ፡ ስጨነቅ ፡ ሆድ ፡ ሲብሰኝ
ከጐኔ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚረዳኝ
ብቻዬን ፡ ያልተውከኝ ፡ ምድረ ፡ በዳ
አለሁኝ ፡ የምትል ፡ ለተጐዳ

አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፬x)

ከወረት ፡ ያልሆነ ፡ ታላቅ ፡ ፍቅርህ
ሀዘኔን ፡ የሚያልፍ ፡ መፅናናትህ
እምባዬን ፡ ያበሰከው ፡ ደጋፊዬ
ስተክዝ ፡ ሆንክልኝ ፡ መፅናኛዬ

አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፬x)

አትከዳኝ ፡ አትለወጥ ፡ በሁኔታ
አተወኝ ፡ ስደክም ፡ ስበረታ
ፍቅርህ ፡ የፍቅሮች ፡ ሁሉ ፡ አውራ
ዘለዓለም ፡ የሚቀጥል ፡ እያበራ

አዝ፦ ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ተመችቶኝ ፡ ነው (፬x)
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መዋል ፡ ማደሩ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)

ሲከፋኝ ፡ ስጨነቅ ፡ ሆድ ፡ ሲብሰኝ (ከአንተ ፡ ጋራ)
ከጐኔ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚረዳኝ (ከአንተ ፡ ጋራ)
ብቻዬን ፡ ያልተውከኝ ፡ ምድረ ፡ በዳ (ከአንተ ፡ ጋራ)
አለሁኝ ፡ የምትል ፡ ለተጐዳ (ከአንተ ፡ ጋራ) (፪x)