Monday, August 8, 2016

ይገባሃልና Yegebahalena ዳንኤል አምደሚካኤል

ዳንኤል አምደሚካኤል Daniel Amdemichael

የጌታዎች ፡ ጌታ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
የይሁድ ፡ አንበሳ ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ
በአምባ ፡ ላይ ፡ ፈረስ ፡ የምትቀመጠው
በክብር ፡ በግርማ ፡ የምትመለሰው
የዘለዓለም ፡ ተስፋችን ፡ ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የደህንነታችን ራስ

አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ

ፊትህ ፡ እንደፀሐይ ፡ በሃይል ፡ ያበራል
ፍቅርህ ፡ ከዕንቁ ፡ ይልቅ ፡ ልብን ፡ ይማርካል
ውበትህ ፡ ያማረ ፡ ክብርህን ፡ ተላብሰሃል
ተመስገን ፡ ጌታችን ፡ ተባረክ ፡ ብለናል
በምድር ፡ ክበር ፡ በሠማይ
ይገባሃልና ፡ መንገሥ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ

አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ

ብዙዎች ፡ ተገዙ ፡ ፍቅርህን ፡ ተረድተው
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያላ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ብለው
ድምጻቸው ፡ ተሰማ ፡ ከየማዕዘኑ
ቅኔን ፡ ተቀኙልህ ፡ በስምህ ፡ የዳኑ
ተመስገን ፡ ተባረክ ፡ ብለው
ዘምረው ፡ አይጠግቡም ፡ ደስታ ፡ ኃይላቸው ፡ ነው

አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ
ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ