ቤተልሔም ተዘራ Bethlehem Tezera
የሚረባኝን ፡ የሚያውቅልኝ (፪x)
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለኝ እኔ ፡ ለራሴ ፡ ደካማ ፡ ነኝ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለኝ እኔ ፡ ለራሴ ፡ አቅምም ፡ የለኝ አፈርኩበት : እኔ ፡ አውቃለው ፡ ባልኩበት እኔ ፡ አውቃለው ፡ ባልኩበት አፈርኩበት ፡ አስቢያለው ፡ ባልኩበት አውቂያለው ፡ ባልኩበት አሁንማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) እንግዲማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) ልጅ ፡ አባቱን ፡ ዳቦ ፡ ቢለው ድንጋይ ፡ ወስዶ ፡ እንዳይሰጠው ሰው ፡ መልካምን ፡ ማድረግ ፡ ካወቀ የእግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ከሰው ፡ የላቅ (፪x) አሁንማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) እንግዲማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) አፈርኩበት : እኔ ፡ አውቃለው ፡ ባልኩበት (፪x) አፈርኩበት ፡ አስቢያለው ፡ ባልኩበት አውቂያለው ፡ ባልኩበት ለቀኑ ፡ ክፋቱ ፡ ይበቃዋል ነገም ፡ ስለ ፡ እራሱ ፡ ይጨነቃል እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ነው ፡ የሚሆነው ዝም ፡ ብሎ ፡ የእርሱን ፡ ማዳን ፡ ማየት ፡ ነው ነፍሴ ፡ አታውኪኝ ፡ አታስጨንቂኝ ፣ ተይ ፡ ተይኝ እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሁንልኝ ፣ ይሁንልኝ (፪x) ነፍሴ ፡ ልምከርሽ ፡ ቁም ፡ ነገር እግዚአብሔር ፡ ስለሚወደው ፡ ነገር ፍቃዴ ፡ ይሁን ፡ ብለሽ ፡ አትደምድሚ ምን ፡ ይላል ፡ ጌታሽን ፡ ተስማሚ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ (፫x) ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ተይ ፡ ኧረ ፡ ተይ ፡ ተይኝ አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፡ (በምህረቱ : ቸርነቱ : የሚከልልሽ) አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ፡ (እንደ ፡ ንስር ፡ የሚያድስ ፡ ቃል ፡ ዋስ ፡ አለብሽ) ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ፡ (ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ) አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ፡ (ታመኝዉ ፣ ታመኝዉ) ተይ ፡ (ታመኝዉ) ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ተይ ፡ (ታመኝዉ) ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ |