Tuesday, August 16, 2016

ብዙ የሆንክልኝ Bezu Yehonkelegn አገኘሁ ይደግ Agegnehu Yideg

አገኘሁ ይደግ Agegnehu Yideg
ክብሬ ፡ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
በመስቀልህ ፡ የሞትከው ፡ ባለውለታዬ
ክብሬ ፡ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ብዙ ፡ የሆንክልኝ ፡ ባለውለታዬ

ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ (፬x)

አዝ፦ ውለታው (፫x)
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ውለታው (፫x)
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ናዝራዊው ፡ ወዳጄ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)

ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ በመስቀል ፡ ሞተልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
በእንጨት ፡ ተንጠልጥሎ ፡ እርግማን ፡ ሆነልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
በከበረ ፡ ደሙ ፡ በውድ ፡ ዋጋ ፡ ገዛኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ሲጠራኝ ፡ ብቻዬን ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አበዛኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)

ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ

አዝ፦ ውለታው (፫x)
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ውለታው (፫x)
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ናዝራዊው ፡ ወዳጄ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)

ከበለስ ፡ ዛፍ ፡ በታች ፡ ተቀምጬ ፡ አይኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ተንኮል ፡ የሌለብህ ፡ የእስራኤል ፡ ልጅ ፡ አለኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ታማኝ ፡ አድርጐ ፡ ቆጥሮ ፡ ለአገልግሎት ፡ ሾመኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ኢየሱሴን ፡ መጠጋት ፡ ለእኔ ፡ እጅግ ፡ ጠቀመኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)

ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ

አዝ፦ ውለታው (፫x)
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ውለታው (፫x)
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ናዝራዊው ፡ ወዳጄ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)

በግ ፡ እረኛ ፡ ነብረኩ ፡ ገና ፡ ብላቴና
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
እግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ አገኘሁኝና
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
እኔን ፡ በናቁኝ ፡ ፊት ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)
ንጉሡ ፡ ሊያከብረኝ ፡ ወደ ፡ እልፊኙ ፡ አገባኝ
(ውለታው ፡ በዛብኝ)

ሰው ፡ ላደረገልኝ ፡ እንደዚህ ፡ ዛሬ
ሥሙን ፡ ላወድሰው ፡ በዝማሬ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ

እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ (፬x)

ክብሬ ፡ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
በመስቀልህ ፡ የሞትከው ፡ ባለውለታዬ
ክብሬ ፡ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ብዙ ፡ የሆንክልኝ ፡ ባለውለታዬ

ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ (፬x)