Wednesday, August 10, 2016

የእኔ ወዳጅ Yenie Wedaj ዳንኤል አምደሚካኤል Daniel Amdemichael #1

ዳንኤል አምደሚካኤል Daniel Amdemichael


አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ/የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)

ከልጅነት ፡ የተሸከመኝ
እስከሽምግልና ፡ የሚመራኝ
አሳዳጊ ፡ ይህ ፡ ወላጅ ፡ የሆነኝ
ያለእርሱ ፡ ወገን ፡ ማነው ፡ ያለኝ

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ/የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)

ቢከፋኝ ፡ ቢደላኝ ፡ እርሱ ፡ ነው
ሁልጊዜ ፡ ከጐኔ ፡ ማገኘው
ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ ወዳጄ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ተቆርቋሪ ፡ ለእኔ

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ/የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)

እግሬን ፡ ከጨለማ ፡ መልሷል
በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ ውስጤን ፡ አስሯል
ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ለእኔ
በፍቅሩ ፡ ተማርካለች ፡ ነፍሴ

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ/የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)

ሕያው ፡ ነው ፡ ምንም ፡ አያረጅም
ዘመን ፡ ሲያልፍ ፡ እርሱ ፡ አይለወጥም
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነው
ታማኝነቱ ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ/የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)

በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)