Wednesday, August 10, 2016

ተስፋ አለው ፊትህን ሳየው Fitehen Sayew ሳሙኤል ተስፋሚካኤል Samuel Tesfamichael #3

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል Samuel Tesfamichael

አዝ፦ ተስፋ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
በረታሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
ደስታ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
ተጽናናሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው (፬x)

አቅም ፡ አጥቼ ፡ ጉልበት ፡ ሲላላ
እምነቴ ፡ ጠፍቶ ፡ ሳይ ፡ ወደኋላ (፪x)
አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው ፡ ብዬ
ከአፌ ፡ ሳልጨርስ ፡ መጣህ ፡ አባብዬ

ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታን ፡ አጠገብከኝና
ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና (፪x)
ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና
ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና

አዝ፦ ተስፋ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
በረታሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
ደስታ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
ተጽናናሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው (፪x)

በመተማመን ፡ የጠበቀህ ፡ ሰው
የሚጐበኝበት ፡ ቀኑ ፡ ቢርቀው (፪x)
በምትዘገይ ፡ ተስፋ ፡ እንዳያዝን ፡ ልቡ
ፈጥነህ ፡ ትደርሳለህ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ አምላኩ

ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታን ፡ አጠገብከኝና
ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና (፪x)
ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና
ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና

አዝ፦ ተስፋ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
በረታሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
ደስታ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው
ተጽናናሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው (፬x)