Monday, August 8, 2016

ዝናዬ Zenayie

ኤፍሬም አለሙ Ephrem Alemu


ልቤ ፡ ሰላም ፡ ሲያጣ ፡ መከራው ፡ ሲበዛ
ወደማን ፡ አያለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ካንተ ፡ ሌላ
ልቤ ፡ ሰላም ፡ ሲያጣ ፡ ወጀቡ ፡ ሲበዛ
ወደማን ፡ አያለሁ ፡ የሱስ ፡ ካንተ ፡ ሌላ

ወየሁ ፡ ጠፋሁ ፡ ብዬ ፡ ሳለቅስ ፡ ሳነባ
ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ብዬ ፡ ስቆዝም ፡ ስከፋ
የዘላለም ፡ አምላክ ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ
የልቤን ፡ ተናግሮ ፡ በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ

አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ
ሚገባኝ ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)

ዝና ፡ ዝናዬ ፡ ዝና ፡ ዝናዬ
አንተው ፡ ነህና (፪x)

ባገልግሎቴ ፡ ላይ ፡ ዝናዬ
ክብር ፡ ያሳየኅኝ ፡ ዝናዬ
የማዕረግ ፡ ልብሴ ፡ ዝናዬ
የክብር ፡ ሽልማት ፡ ዝናዬ

ብኖር ፡ ላትጠቀም ፡ ሞቼ ፡ ላትጎዳ
በደምህ ፡ ከፈልከው ፡ የሕይወቴን ፡ ዕዳ
በደለኛው ፡ ልቤን ፡ በደምህ ፡ ቀድሰህ
ሕይወትን ፡ ሸለምከኝ ፡ ደህንነት ፡ አልብሰህ

ጉድጓዴን ፡ ስቆፍር ፡ ድንበሬን ፡ ልገፋ
ምሕረትህ ፡ ገደበኝ ፡ ታዝቦ ፡ ስገፋ
ነፍሴም ፡ ተመለሰች ፡ ከርስቷ ፡ ግዛት
በመስቀሉ ፡ ስራህ ፡ በጻድቁ ፡ ሞት

አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ
ሚገባኝ ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)

ዝና ፡ ዝናዬ ፡ ዝና ፡ ዝናዬ
አንተው ፡ ነህና (፪x)

ባገልግሎቴ ፡ ላይ ፡ ዝናዬ
ክብር ፡ ያሳየኅኝ ፡ ዝናዬ
የማዕረግ ፡ ልብሴ ፡ ዝናዬ
የክብር ፡ ሽልማት ፡ ዝናዬ

የሰጠኝን ፡ ላጣ ፡ የእጁን ፡ ተመኝቼ
ምሕረትን ፡ ስጠማ ፡ ፍሬዋን ፡ በልቼ
የጽድቅን ፡ ጥያቄ ፡ በልጁ ፡ መልሶ
ፈቃዱን ፡ አጸና ፡ መርገሜን ፡ ፈውሶ

ዝና ፡ ዝናዬ ፡ ዝና ፡ ዝናዬ
አንተው ፡ ነህና (፪x)

ባገልግሎቴ ፡ ላይ ፡ ዝናዬ
ክብር ፡ ያሳየኅኝ ፡ ዝናዬ
የማዕረግ ፡ ልብሴ ፡ ዝናዬ
የክብር ፡ ሽልማት ፡ ዝናዬ