Tuesday, June 13, 2017

ክብር የበቃህ ነህ (Keber Yebeqah Neh) Aster Abebe አስቴር አበበ #1

Aster Abebe አስቴር አበበ #1
አዝ፦ ቀድሞም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ ፡ ግን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈህ
ተገብቶክህ ፡ እንጂ ፡ ማን ፡ ሰቶህ ፡ ያውቃል ፡ ስለጎደለህ
አንሶብህ ፡ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ አደባባይ ፡ ወተህ ፡ ማትለምን
ኢየሱሴ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ምትደነቅ (፪x)

ቀን ፡ አንድ ፡ ተብሎ ፡ ሳይጀመር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ወር ፡ አንድ ፡ ተብሎ ፡ ሳይቆጠር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
ዓመት ፡ በዓመት ፡ ላይ ፡ ሳይደመር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር
በዘመናት ፡ ዘመን ፡ ሳይጨመር ፡ አንተኮ ፡ ስትመለክ ፡ ነበር

አዝ፦ ቀድሞም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ ፡ ግን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈህ
ተገብቶክህ ፡ እንጂ ፡ ማን ፡ ሰቶህ ፡ ያውቃል ፡ ስለጎደለህ
አንሶብህ ፡ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ አደባባይ ፡ ወተህ ፡ ማትለምን
ኢየሱሴ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ምትደነቅ (፪x)

ሳይባል ፡ በመጀመሪያ ፡ ሳትፈጥር ፡ ሰማይና ፡ ምድርን
አዋፋት ፡ ባየር ፡ ላይ ፡ ሳይበሩ ፡ ሳትመሰርት ፡ በፊት ፡ ተራሮችን
ገና ፡ ሳታበጅ ፡ ሰውን ፡ በጅህ ፡ ሳይወጣ ፡ እስትንፋስ ፡ ከአፍህ
ሁሉ ፡ ነገር ፡ ምንም ፡ ባዶ ፡ እያለ ፡ ምሥጋናህ ፡ ግን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈ

አዝ፦ ቀድሞም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ ፡ ግን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈህ
ተገብቶክህ ፡ እንጂ ፡ ማን ፡ ሰቶህ ፡ ያውቃል ፡ ስለጎደለህ
አንሶብህ ፡ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ አደባባይ ፡ ወተህ ፡ ማትለምን
ኢየሱሴ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ምትደነቅ (፪x)

ቀድሞም ፡ ክብር ፡ የበቃህ ፡ ነህ ፡ ግን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈህ
ተገብቶክህ ፡ እንጂ ፡ ማን ፡ ሰቶህ ፡ ያውቃል ፡ ስለጎደለህ
አንሶብህ ፡ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ አደባባይ ፡ ወተህ ፡ ማትለምን
ኢየሱሴ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ምትደነቅ