Tuesday, June 13, 2017

ሥምህን እዘምረዋለሁ Semhen Ezemerewalehu - መስከረም ጌቱ #2

Meskerem Getu  መስከረም  ጌቱ #2
አዝ፦ ሥምህን ፡ እዘምረዋለው (፪x)
ዝናህን ፡ እዘምረዋለው
ሥምህን ፡ እዘምረዋለው
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ እላለሁ
ሥምህን ፡ እዘምረዋለው (፪x)
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ እላለሁ
አንተን ፡ እዘምርሃለው
ስላንተ ፡ መዝሙር ፡ እጽፋለው
ጌታ ፡ እዘምርሃለው
ሁልጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ እላለሁ

በጽድቅ ፡ መጠን ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ያልክ ፡ ነህ
ስምህ ፡ በምድር ፡ የተመሰገነ
ዝናህ ፡ ሁልጊዜ ፡ አስደናቂ ፡ ዜና
ወቅት ፡ የማይሽረው ፡ ዘላለም ፡ ገናና

አዝ፦ ሥምህን ፡ እዘምረዋለው (፪x)
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ እላለሁ
ስላንተ ፡ ቆሜ ፡ አውጃለው
አንተን ፡ እዘምርሃለው
ስላንተ ፡ መዝሙር ፡ እጽፋለው
ጌታ ፡ እዘምርሃለው
በሥምህ ፡ ዜማ ፡ አወጣለው

ከቶ ፡ አይጨልምም ፡ በአንተ ፡ ፊት ፡ ጨለማ
ብርሃንነትህ ፡ ከጫፍ ፡ ጫፍ ፡ ይሰማ
ሞገስ ፡ ግርማህን ፡ ባውጅ ፡ ደጋግሜ
ቃሎች ፡ አነሱ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜ

አዝ፦ ሥምህን ፡ እዘምረዋለው (፪x)
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ እላለሁ
ስላንተ ፡ ቆሜ ፡ አውጃለው
አንተን ፡ እዘምርሃለው
ስላንተ ፡ መዝሙር ፡ እጽፋለው
ጌታ ፡ እዘምርሃለው
በሥምህ ፡ ዜማ ፡ አወጣለው

በሰማያት ፡ ያለኸው ፡ ልቀህ
በልቤ ፡ ላይ ፡ የተጻፍክ ፡ ደምቀህ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ
ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ ስምህን ፡ ላውጅ

ሃሌሉያ (፮x)